Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለኦሊምፒክ ቡድን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

ለኦሊምፒክ ቡድን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

ቀን:

በብራዚል ሪዮ ደጄኔሮ፣ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በሚካሄደው 31ኛው ኦሊምፒያድ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን፣ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ እንደሚሰጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ቃል መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለሪፖርተር እንደገለጸው ከሆነ፣ ዩኒቨርሲቲዎቹና ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ዓርብ ሚያዝያ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በደብረማርቆስ ከተማ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እያካሄዱት ባለው 32ተኛው አገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለውጥ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድኑ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ቀደም ሲል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ለሪዮ ዴጄኔሮ ልኡካን ቡድን ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደሚያስፈልግ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለሪዮ 2016 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ዝግጅትና ተሳትፎ ቀደም ሲል የተጠቀሰውን የገንዘብ አቅም ለማሰባሰብ ባዘጋጀው በዚሁ ፕሮግራም ላይ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶችና ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የማኅበረሰብ አባላት እንዲሳተፉ ስለመደረጉ ጭምር ተገልጿል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያው ፕሮግራሙ የታደሙት የትምህርት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው፣ ‹‹ከአትሌቶቻችን የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት ከዝግጅት እስከ ተሳትፎ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦሊምፒክ ተሳትፎዎች ስናደርግ እንደነበረው ዛሬም ሁለንተናዊ እገዛና ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል፤›› ብለው የትምህርቱ ዘርፍ ለኦሊምፒክ ቡድናችን ያልተቆጠበና የተለመደ አጋርነቱን ሲያደርግ ልዩ ኩራት ሊሰማው የሚገባ መሆኑን ጭምር መግለጻቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ