Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበተመሳሳይ በረራ የተጓዙ 30 ኢትዮጵያውያት ከዱባይ ኤርፖርት ኢሚግሬሽን ተይዘው ተመለሱ

በተመሳሳይ በረራ የተጓዙ 30 ኢትዮጵያውያት ከዱባይ ኤርፖርት ኢሚግሬሽን ተይዘው ተመለሱ

ቀን:

ባለፈው ሳምንት እሑድ ሚያዝያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. በፍላይዱባይ የአየር በረራ በአንዴ ከአዲስ አበባ ከተጓዙት መካከል 30 ኢትዮጵያውያት፣ በዱባይ ኤርፖርት ኢሚግሬሽን የደኅንነት ሠራተኞች ወደ የተባበሩት የዓረብ ኤምሬትስ የንግድ ከተማ ዱባይ እንዳይገቡ ተከልክለው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኘው የፍላይዱባይ የበረራ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ለሪፖርተር እንዳረጋገጠው ከሆነ፣ ሴቶቹ መንገደኞች ሕጋዊ የቪዛና የበረራ ቲኬት ይዘው የተጓዙ ቢሆንም፣ የጉዞ ምክንያታቸው ‹‹ለጉብኝት›› የሚል በመሆኑ ለኤርፖርቱ ኢሚግሬሽን ሠራተኞች አሳማኝ ባለመሆኑ ምክንያት ሊመለሱ ችለዋል፡፡

የአየር መንገዱ ጽሕፈት ቤት እንደሚለው፣ ኤርፖርቱ አንድ ተጓዥ ተመልሶ ወደ አገሩ እንደሚገባ የሚገልጽ የደርሶ መልስ ትኬት መያዙን፣ እንዲሁም በአገሪቱ ለሚኖረው ቆይታው በቂ ስፖንሰር እንዳለው፣ አልያም በቂ ገንዘብ መያዝ አለመያዙን አረጋግጦ ማሳለፍና መከልከል የተለመደ ነው፡፡ ይኼኛውን ድርጊት ለየት የሚያደርገው ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ከአንድ በረራ መመለሱ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ተጓዦቹ ሕገወጥ እንዳልሆኑ ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ዋቢ በማድረግ ገልፍ ኒውስ እንደዘገበው፣ በተለያዩ የበረራ አገልግሎት መስመሮች በየቀኑ በግምት ከ500 በላይ የቤት ሠራተኞች ወደ ዱባይ የሚገቡ ሲሆን፣ በጉብኝት ቪዛ ገብተው እዚያው አገር ለሚገኙ ደላሎችና ኤጀንሲዎች ከፍ ያለ ገንዘብ በመክፈል ቪዛቸውን ወደ ‹‹የሥራ ፈቃድ›› አስቀይረው ይኖራሉ፡፡

ቀደም ሲል በሠራተኛነት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ የሚደረግ ጉዞን የኢትዮጵያ መንግሥት ማገዱ የሚታወስ ሲሆን፣ አዲስ አዋጅ ቢወጣም ሕጋዊ ጉዞ ነገ ዛሬ ይከፈታል ሲባል እስከ ዛሬ እንደተዘጋ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በሕጋዊና በሕገወጥ መንገድ በአየርም በምድርም በርካታ ኢትዮጵያውያት ወደ አካባቢው መጓዝ አለማቆማቸው ይነገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...