Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርሕይወትን ማወቅ ከግጭት ያድናል

ሕይወትን ማወቅ ከግጭት ያድናል

ቀን:

ሕይወት የተፈጥሮ ፀጋ ናት፡፡ መኖር፣ ማደግ፣ ማወቅ፣ መመኘት፣ መሥራት መውደድ፣ ልጅ ወልዶ መሳም፣ ለፍሬ ማድረስ ወዘተ. የሕይወት ገጽታዎች ናቸው፡፡ ሰው ፍላጎቱን የሚያሳካው እንደ ግላዊ ችሎታውና እንደ ማኅበረሰባዊ ግንኙነቱ ቅልጥፍና ነው፡፡ ብቃቱም ሆነ ግንኙነቱ በሥልጣኔ ይሻሻላል፡፡ ሰው በጋራ ጥቅም ላይ ይተባበራል፡፡ በችግር ጊዜ ይረዳዳል፡፡ ሴትና ወንድ እየተፋቀሩ ልጅ ይወልዳሉ፡፡ ዘራቸውን ይተካሉ፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ ስለሚያስበውና ስለሚያውቀው ነገር ሁሉም ሰው አያውቅም፡፡ ሰው እርስ በርሱ ሲነጋገር ግን ይግባባል፡፡ ይኼም ለሰው ልጅ ሕልውና እንደ ኢንሹራንስ ይቆጠራል፡፡

የሰው ልጅ በአብዛኛው ታሪኩ በእኩልነትና በነፃነት ዕጦት ኑሮው ሲተራመስና ሕልውናው ሲደቆስ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያንም እስካሁን ድረስ የዚሁ ገፈት ተቋዳሾች ነን፡፡ አንድ ማኅበረሰብ ራሱን በራሱ መምራት ካልቻለ፣ የዜጎች መብት እንደማይከበር፣ ሽኩቻውም እንደሚቀጥል ግልጽ ነው፡፡ አውሮፓውያን ይኼን የተረዱት ቀደም ብለው በመሆኑ፣ አሁን ላይ የዴሞክራሲ፣ የእኩልነትና የነፃነት ሥርዓት ዘርግተው በተረጋጋ ግንኙነት ውስጥ መኖር ችለዋል፡፡ ለሌሎች አገሮችም ጥሩ ምሳሌ ሆነዋል፡፡ ስንት ዘመን ስንጨቆን ኖረን አለማወቃችን ግን ያሳዝናል፡፡ ‹‹ፀሐዩ ንጉሥ››፣ ‹‹ቆራጡ ኮሚዩኒስት››፣ ‹‹ባለራዕይ ታጋይ›› ወዘተ. ስንላቸው የነበሩት ሁሉ ‹‹ቁርቁዝ አቆርቁዝ›› ነበሩ፡፡ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግን እኛንም ከአረንቋው ያላቅቀናል፡፡ ሕልውናችንን ለማቀጣጠል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት በአግባቡ ማከናወን ይጠቅመናል፡፡

 

1.ዴሞክራሲ ማስፈን

አገር ማለት ሕዝብ አብሮ እየኖረ፣ የኑሮ ፍላጎቱን እያሟላ ሕልውናውን የሚያሰርፅበት ቦታ ነው፡፡ ሕዝብ ሲባል ሴትና ወንድን፣ ሕፃን ልጅን፣ ወጣትን ጎልማሳን፣ አሮጊትና ሽማግሌን ያካተተ ነው፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ዘረመሉ ሁኔታ በባህሪው፣ በመልኩ በቅርፁ በቀለሙ በብልኃቱ፣ በጉልበቱ ወዘተ. ይለያያል፡፡ እናም ኢትዮጵያ አገራችን ይኼን ሁሉ ልዩነት በጉያዋ አቅፋ ነው የምትንቀሳቀሰው፡፡ ውጤታማ የምትሆነውም ዜጎቿ በእኩልነትና በነፃነት እየተንቀሳቀስን የሕልውና ግዴታችንን በዕድሜ በተራችን እየተወጣን ስንኖርና ስንሠራ ነው፡፡ ስለሆነም ሕልውናችንን ለማጠናከር በቅድሚያ የዴሞክራሲ ሥርዓትን ማሥፈን ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ ዴሞክራሲ በሦስት ዋና ተግባሮች ይንፀባረቃል፡፡ ማስተዳደር፣ ሕግ ማውጣትና ሕግ ማስፈጸም፡፡ አስተዳደሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ይመራል፡፡ ሕግ ማውጣት በሕዝብ ተወካዮች፣ ሕግ ማስፈጸም ደግሞ በፍርድ ቤቶች ይፈጸማል፡፡ ሦስት አካላት በልዩነትና እኩልነት ሲንቀሳቀሱ ዜጎች አምራች፣ ትርፋማና ደስተኛ ይሆናሉ፡፡ አገርም ታድጋለች፡፡

2. አምራችነትን ማበልፀግ

ሰው ሕልውናውን ለማስረፅና ለማደስ ጥሩ ምግብ፣ ንፁህ ውኃና አየርጥሩ ልብስ እንዲሁም በምቹ አካባቢ መኖር ያስፈልገዋል፡፡ ዜጋው እነኚህን ነገሮች ሁሉ ለማሟላት እያመረተ ወይም የሚያሟላባቸውን ዘዴዎች እየተጠቀመ ኑሮውን ይገፋል፡፡ ይህ ፀጋ አምላክ ‹‹ጥረህ ግረህ ኑር›› ብሎ ከሰጠን መመርያ የመነጨ ነው ይባላል፡፡ በአሁኑ ዘመን የምግብናሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ምርት አድጓል፡፡ ከአንድ ሄክታር 1000 ኩንታል የእህል ምርት ማግኘት ድሮ ማን ያስብ ነበር፡፡ በሽታና ተውሳኮች በተለያዩ መድኃኒቶችና ዘዴዎች እየተገቱ ነው፡፡ የሰው ዕድሜ ጨምሯል፡፡ በሠለጠኑ አገሮች አማካኝ ዕድሜ ወደ እስከ 90 ዓመት እየሆነ ነው ይባላል፡፡ እኛም ወደ 60 ዓመት እንደገባን ይነገራል፡፡ ወደ ጨረቃና ፕላኔቶችም መወንጨፉ ቀጥሏል፡፡ የሰው ልጅ አድማሱ ሰፊ ነው፡፡ ዕይታውም ብሩህ ነው፡፡

3. የሕዝብ ብዛትን መመጠን

አዳምና ሔዋንን አምላክ ‹‹ብዙ ተባዙ ዓለምን ሙሏት›› ብሎ እንደመረቃቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡ በአዳም ዘመን ሰው ጥቂት ነበር፡፡ አሁን ግን በዝቷል፡፡ ሰባት ቢሊዮን አልፏል፡፡ ምድር ሞልታለች፡፡ ሽሚያና ሽኩቻው ግሏል፡፡ ታዋቂው ተመራማሪ ቶማስ ማልተስ በታወቀውና የማልተስ ንድፈ ሐሳብ እየተባለ በሚታወቀው ሥራው እንደጠቀሰው፣ የሕዝብ ብዛት በዘዴ ወይም በተፈጥሮ ችግር (በሽታ፣ ረሃብጦርነት) ካልተገታ በቀር፣ ሰፊ ድህነትና የተፈጥሮ ሀብት ብክነት ይደርሳል፡፡

በእንዲህ ያለው ችግር ምክንያት በእኛ አገር ድህነት ሥር ሰዷል፡፡ የተፈጥሮ ሀብት በእጅጉ ባክኗል፡፡ ስደቱም በዝቷል፡፡ የሠለጠኑት አገሮች ግን የተሻለ ዘዴ ቀይሰዋል፡፡ ‹‹ራስህን ተካ›› በሚል ሥርዓት ብዛታቸውን እየተቆጣጠሩ የተሻለና የተረጋጋ ኑሮ ይመራሉ፡፡ እኛ ብቻን ሳንሆን በበርካታ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በጋብቻ ላይ ጋብቻን የሚያበራታታ ባህልና ሃይማኖት ስለምንከተል፣ ለቤሰተብ ምጣኔና ለስነ ተዋልዶ ያለን ግንዛቤም አነስተኛ በመሆኑ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ በርካታ ልጆች እየወለድን ለሽኩቻናግጭት እንዳረጋለን፡፡

4. የኑሮ ሽሚያን በዘዴ መፍታት

ሰው ለኑሮው በሚፈልገው ነገር ሁሉ ከብጤው ጋር ይሻማል፡፡ የሥነ ሕይወት ተመራማሪው ዳርዊን እንዳለው፣ ሽሚያ በቅርብ ዘመዳሞች መካከል ይብሳል፡፡ ይኸውም ፍላጎታቸው ስለሚመሳሰል ነው፡፡ ሽሚያወደ ግጭት ይወሰዳል፡፡ በግጭቱ የተጎዳ ሰው ቂም ያበቀላል፡፡ ይቋጥራል፡፡ በቂም በቀል ብድሩን ይመልሳል፡፡ ቂም በቀል በዘዴ ካልተገታ መግቻ ልጓም ላይኖረው ይችላል፡፡ ችግሩ ግን በዴሞክራሲ ሥርዓት በቀላሉ ይፈታል፡፡ አድሎ የሌለው የፍትሕ ሥርዓት ካለ፣ ያጠፋው ዜጋ በሕግ ይቀጣል፡፡ ቂም በቀሉም በዚህ ያለው ዘዴ ያደርቃል፡፡ በዚህ ሒደት ‹‹ነገርን በነገር አትፍቱ፣›› የሚለው ክርስቶሳዊ ትምህርት ተግባር ላይ ዋለ ማለት ነው፡፡

6. ዕውቀትን ማበልፀግ

ተፈጥሮ ሒደቷ ግልጽ አይደለም፡፡ በዕለት ኑሮ ሒደት ምን እንደሚያጋጥም ማንም አያውቅም፡፡ ሆኖም ግን ኑሮ መመራት ያለበት በዕውቀት ቢሆን ይመረጣል፡፡ ተፈጥሮ ረዥም ዕድሜ አላት፡፡ አጀማመሯም ከቁስ አካል እንደሆነ ይገመታል፡፡ ቁስ አካል ወደ ኢነርጂ፣ ኢነርጂም መልሶ ወደ ቁስ አካልነት ይለወጣል ይባላል፡፡ ማንኛውም የተፈጥሮ እንቅስቃሴ ከቁስ አካልና ከኢነርጂ ጋር ሲጋጩ ውህዶች ይፈጠራሉ ወይም ይፈርሳሉ፡፡ ሕይወትም የመስተፃምሩ ፍሬ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በመሆኑም የሰው አኗኗር፣ አካባቢውን በማወቅና በመረዳት ሲሆን ኑሮው የቀለለና የተሰከነ ይሆናልና ዕውቀት ይቅደም፡፡

(ፍቅሩ አማረ፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...