Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የሥራ ዕድልና ለታክስ ማሻሻያ ፕሮግራም የሚውል የአራት ቢሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጠች

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችም ከዕርዳታው ተጠቃሚ ይሆናሉ

የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ብሎም ለታክስ ሥርዓቱ ማሻሻያ ፕሮግራም ድጋፍ የሚውል የ115 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም የ4.025 ቢሊዮን ብር ዕርዳታ ሰጠ፡፡

በእንግሊዙ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋም (ድፊድ) እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መካከል በተፈረመው ስምምነት መሠረት፣ የ80 ሚሊዮን ፓውንድ ዕርዳታው ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የሥራ ዕድል ፈጠራ መስኮች የሚውል ነው፡፡ ቀሪው 35 ሚሊዮን ፓውንድ ደግሞ በአብዛኛው በእንግሊዝ መንግሥት ተቋማት ድጋፍ እየተደረገለት ለሚገኘው የታክስ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም ትግበራ እንዲውል ስምምነት ተደርጓል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋምን በመወከል ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ጋር የፋይናንስ የመግባቢያ ስምምነት የፈረሙት ሚስስ ፔኒ ሞርዳንት ናቸው፡፡ ሚስስ ሞርዳንት የእንግሊዝ ፓርማ አባልና የዓለም አቀፍ ልማት ምክትል ሚኒስትር እንዲሁም የእኩልነትና የሴቶች ጉዳዮች ሚኒስትር ናቸው፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ መንግሥት እያስፋፋቸው በሚገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮችና በሌሎችም መስኮች ከሚያፈልገው የሰው ኃይል ውስጥ ለ100 ሺሕ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችልበትን ዕገዛ ለማድረግ የሚውል የዕርዳታ ገንዘብ ከእንግሊዝ መንግሥት አግኝቷል፡፡ ይሁንና ዕርዳታው ለ30 ሺሕ ስደተኞችም የሥራ ዕድል በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ እንደሚውል በስምምነቱ መካተቱን ሚኒስትር ተከስተ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከሆነ መንግሥት ከሁለት ዓመታት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባዔ ወቅት ይፋ ባደረገው መሠረት፣ ኢትዮጵያ በምታካሂደው የኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ዕቅድ ውስጥ ከሚፈጠሩት የሥራ ዕድሎች ውስጥ በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችም የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በመሆኑም 30 ሺሕ ስደተኞች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥም የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግ መነሳቱን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ ዲፊድ በድረ ገጹ እንዳሰፈረው መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ከ890 ሺሕ በላይ የደቡብ ሱዳን፣ የሶማሊያ፣ የሱዳንና የኤርትራ ስደተኞች በተለያዩ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ይህ የስደተኞቹ ቁጥር ኢትዮጵያን በአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የስደተኞች መጠለያ አገር እንደሚያሰኛት ተቋሙ ይጠቅሳል፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት ከዚህ ቀደም ይከተል የነበረውን የዕርዳታ አሰጣጥ በአዲስ አሠራር መተካቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ይኸውም የሚሰጠው ዕርዳታ በፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የተመሠረተና በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በተግባር መከናወን በተቻለው የሥራ መጠን እየተለካ የሚለቀቅ የዕርዳታ አሰጣጥ እንደሚከተል አስታውቆ ነበር፡፡ የዕርዳታ አሰጣጡ መንገድ ከዚህ ቀደም ከነበረው አካሄድ እንዲቀየር የተደረገው በፖለቲካዊ ምክንያቶች እንደሆነ በሰፊው ሲዘገብ መቆየቱም አይዘነጋም፡፡

ይሁንና ሚኒስትሯ ሞርዳንት እንዳስታወቁት፣ መንግሥታቸው ኢትዮጵያ ለሚያስፈልጓት የልማት ሥራዎች ድጋፉን መስጠቱን አያቋርጥም፡፡ በታክስ አሰባሰብና ረገድ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ አገሮች ከኢኮኖሚው አኳያ ያለው ድርሻ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እስከ 13 በመቶ እንደነበር ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ይኼንን የሚያሻሽል የታክስ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራም መተግበር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ማሻሻያው የሕግ ማዕቀፎችን ጨምሮ በታክስ ኦዲትና በመሳሰሉት መስኮች ለውጦች ማድረግ መጀመሩም ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች