Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምአዲሱ የለንደን ከንቲባ ሥጋትና የዶናልድ ትራምፕ ምልከታ

አዲሱ የለንደን ከንቲባ ሥጋትና የዶናልድ ትራምፕ ምልከታ

ቀን:

‹‹የለንደን ከንቲባ ሆኜ መመረጤ በእስልምናና በምዕራቡ ዓለም መካከል የሥልጣኔ ግጭት እንደሌለ አሳይቷል፡፡ ምዕራባዊ ነኝ፡፡ እንግሊዛዊና የለንደን ነዋሪም፡፡ እምነቴ እስልምና፣ መነሻዬ እስያ ሆኖ የዘር ግንዴ ከፓኪስታን ነው፡፡ አይኤስም ሆነ ሌሎች የአኗኗር ዘይቤያችንን ለማጥፋት የሚመኙና ስለምዕራባውያን የሚያወሩ ስለእኔም እያወሩ ነው፡፡›› አዲሱ የለንደን ከንቲባ ሳዲቅ ክሃን ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡

ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያው ሙስሊም የለንደን ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ሳዲቅ ክሃን፣ የከንቲባነት ሥልጣን መቆናጠጣቸውን ተከትሎ ከታይም መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አክራሪነትንና ፅንፈኝነትን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን የሚያረክሱ መድኃኒት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የ45 ዓመቱ ክሃን በአውሮፓ የተዋጣላቸው ሙስሊም ፖለቲከኛ ይሆናሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን፣ እሳቸውም ይህንኑ ለማጠናከር ለአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የሚከተሉት የፖለቲካ አቅጣጫ ትክክል እንዳልሆነ ለመምከር፣ ወደ አሜሪካ ማቅናት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ክሃን እንደሚሉት፣ አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ2016 ማብቂያ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው የሚጠበቁት ቢሊየነሩ ትራምፕ ሥልጣን ሳይቆናጠጡ፣ አሜሪካ አቅንተው በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መምከር ይፈልጋሉ፡፡

የአሜሪካን የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ከተቆናጠጡ ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ ገደብ እንደሚጥሉ የሚናገሩት ትራምፕ፣ በአቋማቸው የብዙ አሜሪካውያንን ድጋፍ እያገኙ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ደግሞ የለንደኑን ከንቲባ ክሃንን ጨምሮ ለሌሎች ሙስሊሞችም የአሜሪካ በር ይዘጋል፡፡ ይህን ከሚቃወሙ ፖለቲከኞች ጎራ አዲሱ የለንደን ከንቲባ ክሃን ተቀላቅለዋል፡፡

‹‹ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ በሃይማኖቴ ምክንያት አሜሪካ እንዳልገባ እከለከላለሁ፤›› ያሉት ክሃን፣ የትራምፕ የፖለቲካ አቅጣጫ አሜሪክሃን የትም አያራምዳትም ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አዲሱ ከንቲባ ከሥጋታቸው የተነሳም በቅርቡ የመጀመሪያ ጉዞዋቸውን ወደ አሜሪካ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ በሙስሊሞች ላይ ያላቸው አቋም አክራሪ የሚያስብላቸው ቢሆንም፣ የለንደኑን ከንቲባ ክሃን በተመለከተ የአሜሪካ በር በልዩ ሁኔታ እንደሚከፈትላቸው ተናግረዋል፡፡ ለክሃን ያላቸውን አመለካከትም የገለጹት፣ ‹‹ክሃን የለንደን ከንቲባ ሆኖ በመመረጡ ደስተኛ ነኝ፤›› በማለት ነው፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡም ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ በማለት ያቀረቡት ሐሳብ፣ ክሃንን በተመለከተ በልዩ ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል ነው፡፡

በፓሪስ 130 ሰዎችን የቀጠፈውን የሽብር ጥቃት ተከትሎ ፕሬዚዳንት ቢሆኑ ሙስሊሞች አሜሪካ እንዳይገቡ እንደሚያግዱ የተናገሩት ትራምፕ፣ ክሃንን አስመልክቶ ‹‹ሁል ጊዜም በልዩ ሁኔታ የሚታዩ ጉዳዮች አሉ፤›› ብለዋል፡፡

ትራምፕ ሙስሊሞች ላይ ባላቸው አመለካከት ከአሜሪካም ሆነ ከአሜሪካ ውጪ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም፣ በአገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በሚካሄዱ ቅድመ ምርጫ ትንበያዎች ከ30 እስከ 50 በመቶ በሚዋዥቁ መራጮች ድጋፍ እያገኙ ነው፡፡ እሳቸውም ያቀረቡት ሐሳብ ለአሜሪካ ደኅንነት ወሳኝ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆነው ቢመረጡ የለንደኑ ከንቲባ ክሃን በልዩ ሁኔታ አሜሪካ መምጣት እንደሚችሉ ቢናገሩም፣ ክሃን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዕጩ የሆኑትን የትራምፕ ‹‹በልዩ ሁኔታ ይታያል›› ግብዣ አጣጥለውታል፡፡

‹‹ጉዳዩ የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የጓደኞቼ፣ የቤተሰቦቼ እንዲሁም የእምነቱ ተከታይ የሆኑና ከየትኛውም አካባቢ የሚመጡ ሕዝቦች ጭምር ነው፤›› ብለዋል፡፡ እሳቸው ትራምፕ በእስልምና ላይ ያላቸው ጭፍን አመለካከት አሜሪካና እንግሊዝን አደጋ ውስጥ ይከታል የሚል ሥጋት ቢኖራቸውም፣ ትራምፕ ለክሃን ሥጋት ቦታ አልሰጡትም፡፡

ትራምፕ የእስልምና እምነት ተከታዮች አሜሪካ ከመግባት ለተወሰነ ጊዜ ታግደው ሁኔታዎች መታየት አለባቸው በሚለው አቋማቸው ፀንተዋል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ብዙ ሙስሊሞች በአሜሪካ ላይ ጥላቻ አሳድረዋል የሚል ነው፡፡

በአክራሪነት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን እፈታለሁ ለሚሉት ክሃን ይህ የሚዋጥ አይደለም፡፡ ዕጩው ትራምፕ የአሜሪክሃን የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን መያዝና አመለያዛቸው ሳይታወቅ ሥጋትም ገብቷቸዋል፡፡

የትራምፕ አካሄድ በዓለም የሚገኙ ሙስሊሞችን የሚያገልና በአክራሪዎች እጅ እንደመጫወት የሚቆጠርም ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ትራምፕና በዙሪያው ያሉ ሰዎች የምዕራባውያኑ ለዘብተኛ አመለካከት ከአብዛኛው ሙስሊም ጋር አይጣጣምም ቢሉም፣ ይህ እውነት እንዳልሆነ ለንደን መስክሯል፤›› ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ሊበራሉ ክሃን ከወግ አጥባቂው ዛክ ጎልድስሚዝ ጋር ለለንደን ከንቲባነት ሲወዳደሩ ክሃን እንዳይመረጡ ቅስቀሳ የተደረገው፣ ትራምፕ በሙስሊሞች ላይ እጥለዋለሁ ያሉት አሜሪካ የመግባት ገደብ ነበር፡፡ ሆኖም ክሃን 1,310,143 ድምፅ በማግኘት 994,614 ያገኙትን ጎልድስሚዝ ረትተዋል፡፡

ወግ አጥባቂዎች ክሃንን ለመጣል የተጠቀሙበት ዘመቻም አግባብ እንዳልነበር የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ክሃንም ቢሆኑ ሃይማኖትንና ዘርን ለምርጫ ቅስቀሳ መጠቀም አደጋው የከፋ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...