Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ አየር መንገድን አውሮፕላን የጠለፈው ረዳት አብራሪ አስገዳጅ የአዕምሮ ሕክምና እንዲደረግለት ተወሰነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን አውሮፕላን የጠለፈው ረዳት አብራሪ አስገዳጅ የአዕምሮ ሕክምና እንዲደረግለት ተወሰነ

ቀን:

ከሁለት ዓመት በፊት ያበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ፣ አስገዳጅ የሆነ ክትትል የሚደረግበት የአዕምሮ ሕክምና እንዲደረግለት የስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ወሰነ፡፡

የስዊዘርላንድ የዜና ወኪሎች እንደዘገቡት ጄኔቭ የሚገኘው የፌዴራል ወንጀል ፍርድ ቤት ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት የኃይለ መድኅን አበራ የአዕምሮ ሕመም የማገርሸት ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣ በካንተን ጄኔቫ ጥበቃ እየተደረገለት የአዕምሮ ሕክምና እንዲደረግለት አስገዳጅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ኃይለ መድኅን ‹‹ፓራኖይድ ስኪዞ ፌሬኒያ›› የሚባል ሕክምና ክትትል በማድረግ ላይ በመሆኑ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለመስማት ችሎት እንዳልቀረበ የዜና ወኪሎች ዘግበዋል፡፡

የኃይለ መድኅን የመከላከያ ጠበቆች ደንበኛቸው አውሮፕላኑን በሰላም በማሳረፍ የመንገደኞቹን ሕይወት ለአደጋ ያላጋለጠ በመሆኑ በነፃ እንዲሰናበት መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ ኃይለ መድኅን በወቅቱ ከአዲስ አበባ 193 መንገደኞችን አሳፍሮ ወደ ሮም ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ዋና አብራሪ ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄድ፣ የአውሮፕላኑን አቅጣጫ በመለወጥ ጄኔቫ ማሳረፉና የስዊዘርላንድ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጠው መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የስዊዘርላንድ የፌዴራል ወንጀል ችሎት የኃይለ መድኅን የአብራሪነት ፈቃድ እንዲሰረዝ፣ አቅሙ ሲፈቅድ ለክርክር የወጣውን 3,000 የስዊዘርላንድ ፍራንክ (3,092 ዶላር) እንዲከፍል ወስኖበታል፡፡

የፍርድ ሒደቱ ሲጀመር ኃይለ መድኅን በአውሮፕላን ጠለፋ እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ይወሰንበታል የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም፣ የስዊዘርላንድ ፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ረዳት አብራሪው አውሮፕላን በጠለፈበት ወቅት ‹‹ፓራኖያ›› በሚባል የአዕምሮ ሕመም ላይ የነበረ በመሆኑ አግባብ የሆነ ዕርምጃ ሊወስድ የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልነበር ከድምዳሜ ላይ በመድረሱ ከቅጣት ሊተርፍ ችሏል፡፡ በመሆኑም ረዳት አብራሪው እስካሁን ጥበቃ በሚደረግለት የአዕምሮ የሕክምና ማዕከል ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ጠላፊው ተላልፎ እንዲሰጠው ያቀረበውን ጥያቄ የስዊዘርላንድ ባለሥልጣናት ባለመቀበል በስዊዘርላንድ ፍርድ ቤት እንዲዳኝ አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኃይለ መድኅንን በአውሮፕላን ጠለፋ ወንጀል በሌለበት የ19 ዓመታት የእስር ቅጣት እንደወሰነበት ይታወሳል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...