Monday, June 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በ2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ላለፉት ስድስት ዓመታት በእንግሊዝና በአይስላንድ ኩባንያ ካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ሲገነባ የቆየው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ግንባታው ተጠናቅቆ እሑድ ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ይመረቃል፡፡

በዓመት 185 ጊጋ ዋትስ በሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለሚሰጠው ለዚህ ፕሮጀክት፣ በንዑስ ተቋራጭነት የቻይናው ሲኤንኤኢሲ (CNAEC) ኩባንያ ተሳትፏል፡፡ ራምቦ ዴንማርክ የተባለው ድርጅትም በአማካሪነት ሠርቷል፡፡

ለፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየቀኑ 1,400 ቶን ደረቅ ቆሻሻ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር ተስማምቷል፡፡

በፕሮጀክቱ ላይ 1,300 ኢትዮጵያዊያንና 286 የውጭ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ የመጀመርያው የሆነው ይኼ ፕሮጀክት ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግሥት የተሸፈነ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች