Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑ ብሔራዊ አትሌቶችን ይፋ አደረገ

ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ አትሌቶችን ይፋ አደረገ

ቀን:

በመጪው ነሐሴ ክረምት የሚካሄደው 31ኛ ኦሊምፒያድ ሊጀመር 82 ቀን ብቻ ቀርቶታል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በጊዜያዊነት የመረጣቸውን ብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ ከአጭር ርቀት ጀምሮ እስከ ማራቶን 66 አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ በሥልጠና ላይ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

እንደ ፌዴሬሽኑ መግለጫ ከሆነ፣ በአሁኑ በምርጫው ተካተው ብሔራዊ ዝግጅት በማድረግ ላይ ከሚገኙ አትሌቶች መካከል ወቅታዊ አቋማቸው እየታየ በሒደት የሚቀነሱ ወይም የሚጨመሩ ሊኖሩ የሚችልበት ሁኔታ እንደሚኖርም አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት በወንዶች 10,000 ሜትር ሙክታር እንድሪስ፣ ኢማና መርጊያ፣ ሞሰነት ገረመው፣ አዱኛ ታከለ፣ ፀበሉ ዘውዴ፣ ታምራት ቶላ፣ ሙሴ ዋሲሁን፣ ይገረም ደመላሽ፣ ኢብራሒም ጀይላ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ታሪኩ በቀለና ብርሃኑ ለገሰ ሲሆኑ፣ በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገለቴ ቡርቃ፣ በላይነሽ ኦልጅራ፣ ዓለሚቱ ሀሮዬ፣ ነፃነት ጉደታና ጎይቶቶም ገብረ ሥላሴ ሆነዋል፡፡

በ5,000 ሜትር ወንዶች፣ ዮሚፍ ቀልጀልቻ፣ ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ደጀን ገብረመስቀል፣ የኔው አላምረው፣ ያሲን ሃጂ፣ ልዑል ገብረ ሥላሴና ጌታነህ ሞላ ሲሆኑ፣ በሴቶች አልማዝ አያና፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ መሠረት ደፋር፣ ዓለሚቱ ሐዊና ሐብታምነሽ ተስፋዬ ናቸው፡፡

1,500 ሜትር ወንዶች አማን ወጤ፣ ዳዊት ወልዴ፣ አማን ቃዲ፣ በቀለ ጉተማና መኮንን ገብረመድህን ሲሆኑ፣ በሴቶች ደግሞ ዳዊት ሥዩም፣ ጉደፋይ ፀጋዬ፣ ባሶ ጎዶና አክሱማዊት አምባዬ ናቸው፡፡

800 ሜትር ወንዶች መሐመድ አማን፣ ጃና ኡመር፣ ማሙሻ ሌንጮና ዮብሷን ግርማ ሲሆኑ፤ በሴቶች ትዕግሥት አሰፋ፣ ሀብታም ዓለም፣ ጫልቱ ሹሜና ሊዲያ መለስ መሆናቸው ታውቋል፡፡

3,000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ብዙአየሁ መሐመድ፣ እቴነሽ ዲሮ፣ ብርቱካን ፈንቴ፣ ሶፍያ አሰፋ፣ ሕይወት አያሌውና ወይንሸት አንሳ ሲሆኑ፣ ወንዶች አምሳሉ በላይ፣ ኃይለ ማርያም አማረ፣ ታደሰ ሰቦቃ፣ ጫላ ባዩ፣ ጅግሳ ቶሎሳና ጌትነት ዋለ ናቸው፡፡ በተያያዘም ፌዴሬሽኑ በአጭር ርቀት 400 ሜትር ሴቶች ትዕግሥት ታማኙና ማህሌት ፍቅሬ፣ እንዲሁም በወንዶች አብዱርአህማን አብዶና ገመቹ ዓለሙ መመረጣቸውን አስታውቋል፡፡ የማራቶን ተወዳዳሪዎችን በተመለከተ ደግሞ ከግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. በኋላ ዝርዝሩ ይፋ እንደሚሆን ገልጿል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ