Friday, July 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን በዚህ ወር ሊጎበኙ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የቀድሞ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሴት ልጅ የሆኑት የወቅቱ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጊዩን ሒ፣ በዚህ ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ መረጃዎች አመለከቱ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮችና የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መግለጫ እንደሚያረጋግጠው ፕሬዚዳንቷ እ.ኤ.አ. ከሜይ 25 ቀን 2016 ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚያደርጉት የአፍሪካ ጉብኝት ኢትዮጵያ የተካተተች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጎበኟቸው አገሮች ኡጋንዳና ኬንያ መሆናቸውን መረጃዎቹ ያመለከቱ ሲሆን፣ በጉብኝታቸው ወቅትም የመንግሥታቸውን አዲስ የልማት ዕርዳታ ፕሮግራም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የልማት ዕርዳታ ፕሮግራሙ ‹‹Korea Aid›› የሚባል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ በኮሪያ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ሥር ይመራል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ጉብኘታቸው ወቅትም በአፍሪካ ኅብረት በመገኘት የመንግሥታቸውን የአፍሪካ ፖሊሲ በተመለከተ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንቷ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን  የያዙት እ.ኤ.አ. በ2013 በምርጫ አሸንፈው ሲሆን፣ ታዋቂው የፎርብስ መጽሔት በዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ካላቸው ሴቶች መካከል በ13ኛ ደረጃ ላይ ሠፍረዋል፡፡

   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች