Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በዘመን ባንክ ላይ ቀርቦ የነበረ የ10.3 ሚሊዮን ብር ክስ ውድቅ ተደረገ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የዘመን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ሁለት መሥራችና አደራጆች አክሲዮን ማኅበሩ ከነወለዱ 10,359,105 ብር እንዲከፍላቸው ለፍርድ ቤት ያቀረቡት የፍትሐ ብሔር ክስ፣ ግንቦት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ውድቅ ተደረገ፡፡

የመሥራችነት ጥቅም እንደሚገባቸው የተጠቀሰውን ገንዘብ የጠየቁት አቶ ኤርሚያስ አመልጋና አቶ ተክሌ ዓለምነህ ሲሆኑ፣ የጠየቁት የመሥራችነት ጥቅም ባንኩ በሦስት ዓመታት ውስጥ ካተረፈው 100 ሚሊዮን ብር ከሚጠጋ ገንዘብ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

ጠያቂዎቹ በባንኩ ላይ ያቀረቡትን ክስ የመረመረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ዘጠነኛ ከፍተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ክሱን ውድቅ ያደረገበትን ምክንያት እንዳስረዳው፣ መሥራቾች ከባንኩ ትርፍ ላይ የመሥራችነት ጥቅም ሊያገኙ የሚችሉት የትርፍ ድርሻቸው በባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ ፊርማ ሲፀድቅ መሆኑን በመግለጽ ዘመን ባንክ መከራከሩን ጠቁሞ፣ ፍርድ ቤቱም በማረጋገጡ ነው፡፡

ጠያቂዎቹም መሥራቾች የመሥራችነት ጥቅም ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ጠቅላላ ጉባዔው ያፀደቀበትን የሰነድ ማስረጃ አለማቅረባቸውንም ፍርድ ቤቱ አክሏል፡፡

ዘመን ባንክ ሌላው ያቀረበው መከራከሪያ እነ አቶ ኤርሚያስ የመሥራችነት ጥቅም ሊከፈላቸው እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ ስማቸው መሥፈሩ ወይም በፕሮስፔክተስ (የፕሮግራም መግለጫ) ላይ መጠቀሱ፣ በመመሥረቻ ጽሑፍ ላይ ‹‹መሥራች ከትርፍ ድርሻ ላይ ይካፈላል›› መባሉ ብቻ ትርፍ እንዲካፈሉ መብት እንደማያሰጣቸው መግለጹን ፍርድ ቤቱ አስረድቶ፣ ክሱን ውድቅ ለማድረግ ሌላው ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡

አቶ ኤርሚያስ በውል አቶ ተክሌ ደግሞ በደመወዝ ሠራተኛ ሆነው በምሥረታ ወቅት አገልግሎት በመስጠታቸው እንደ መሥራች ወይም አደራጅ ተቆጥረው የትርፍ ድርሻ ተጠቃሚ ለመሆን፣ በተለየ ዝርዝር ተቀምጦና ለአገልግሎቸው ሊከፈላቸው የሚገባ በጠቅላላ ጉባዔ ፊርማ ሊረጋገጥ እንደሚገባ ፍርድ ቤቱ ከክርክሩ መረዳቱን ገልጿል፡፡ ከላይ የተገለጸው ሁኔታ ባልተሟላበት ሒደት ሁለቱም ከሳሾች ያቀረቡት የመሥራችነት ጥቅም ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጾ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ክሱንም ውድቅ በማድረግ ዘመን ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፍርድ ቤት በመመላለስ ለተጉላላበት ወጪና ኪሳራ 20 ሺሕ ብር እንዲከፈለው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የእነ አቶ ኤርሚያስ ጠበቃ አቶ ዮሴፍ አዕምሮ ግን በፍርድ ቤቱ ውሳኔ አይስማሙም፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ የመሥራችነት ጥቅምን በሚመለከት (Founders Benefits) በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብና በንግድ ሕጉ የተደነገገ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት እንዲከፈላቸው በፊርማቸው ማረጋገጣቸውንም አክለዋል፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳን የሥር ፍርድ ቤት ክሱን ውድቅ ያደረገ ቢሆንም፣ የይግባኝ አቤቱታቸውን ለይግባኝ ሰሚው ችሎት እንደሚያቀረቡ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች