Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለድርቁ መቋቋሚያ ከለጋሽ አገሮች ከተጠየቀው 54 በመቶ ብቻ ተገኘ

ለድርቁ መቋቋሚያ ከለጋሽ አገሮች ከተጠየቀው 54 በመቶ ብቻ ተገኘ

ቀን:

– የአሜሪካ መንግሥት ተጨማሪ ለ128 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

በአገሪቱ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይገኛል ተብሎ ከሚጠበቀው የ1.4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ውስጥ፣ ከስምንት ወራት በኋላ 54 በመቶ ብቻ የሚሆነው ድጋፍ መገኘቱን መንግሥት አስታወቀ፡፡ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ዓርብ ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፣ የአብዛኛዎቹ አገሮች መንግሥታትና ለጋሽ ተቋማት ቃል የገቡትን አልፈጸሙም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በይፋ በድጋሚ ጥሪ ሊያቀርብ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነር ምትኩ እንዳሉት፣ መንግሥት በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ላልሆኑ አቅርቦቶች ከ381 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድቦ እየሠራ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሕይወት መታደግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኮሚሽነሩ ይኼንን የገለጹት የአሜሪካ መንግሥት ለድርቁ የሚውል ተጨማሪ የ128 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መስጠቱን ይፋ ለማድረግ በኮሚሽነሩ ጽሕፈት ቤት በተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) በኩል የተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ፣ በአገሪቱ ባለፉት 50 ዓመታት ከታዩት አስከፊ የተባለውን ድርቅ ለመቋቋም የሚያግዝ መሆኑን የኤጀንሲው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ 

ድርቁ በተከታታይ በቂ ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የተከሰተ ሲሆን፣ በድርቁ የተጎዱ ወገኖች የዕለት ዕርዳታ ጠባቂ ሆነዋል፡፡ በዕለቱ የተደረገው ተጨማሪ ሰብዓዊ ዕርዳታ የንፁህ መጠጥ ውኃ፣ የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎትና ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድንን ያካተተ ወሳኝ የሆነ ድጋፍ ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ተረጂዎች በቀጣዩ የዝናብ ወቅት የምግብ እህል ለማምረት የሚያስችላቸውን ዘር እንዲያገኙ እንደሚያስችልም ተገልጿል፡፡

 የዲሞክራሲ፣ የግጭትና የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ተጠባባቂ ረዳት አስተዳዳሪ ቶማስ ኤች ስቶል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ጋር በመሆን አዲሱን የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል፡፡ ስቶል በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፣ ‹‹ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የአሜሪካ መንግሥት ድርቁ ወደ ብሔራዊ ሰብዓዊ ቀውስ ደረጃ እንዳይሸጋገር  ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፤” ብለዋል፡፡

 የአሁኑን የገንዘብ ድጋፍ ጨምሮ የአሜሪካ መንግሥት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2014 ጀምሮ በአጠቃላይ 705 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡ በዚህም አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛውን የሰብዓዊ ዕርዳታ የምታደርግ አገር መሆኗን ቀጥላለች፡፡

 አሜሪካ ለድርቁ ተገቢውን ልገሳ ያደረጉ ለጋሾችን የምታደንቅ መሆኗን፣ ሌሎችም የድርቁን ተፅዕኖ ለመቋቋምና በብዙ መስዋዕትነት የተገኘውን ልማት ለመታደግ የተጀመረውን ዓለም አቀፍ ጥረት እንዲቀላቀሉ እንደምታበረታታ ትገልጻለች፡፡

በተያያዘ ዜናም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ሐሙስ ግንቦት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት፣ መንግሥት ደራሽ ጎርፍ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ አስከፊ አደጋ ከማድረሱ በፊት ለመከላከል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ጎርፉ የሚያደርሰውን ጉዳት አስቀድሞ ለመከላከል በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጥ መቆየቱንም ጨምረው አስረድተዋል።

በተለይ ድርቅ ባጠቃቸው አካባቢዎች ዝናብ ባይዘንብ እንኳን የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ በመሆኑ ከማስጠንቀቂያ በተጨማሪ፣ ከተሞች አካባቢ የተደፈኑ የውኃ መውረጃ ቱቦዎች እንዲከፈቱና ለአደጋው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች እንዲነሱ ማድረግ ተጀምሯል።

እስካሁን ድረስ በጎርፍ አደጋ 100 ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ አደጋው ከዚህ የባሰ ጉዳት እንዳያስከትልና በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ የተጀመረው ጥረት ይጠናከራል ብለዋል።

‘’ጎርፍ የቱንም ያህል ዝግጅት ቢደረግ የማይቀሩ አደጋዎች ይኖሩታል፤’’ ያሉት ሚኒስትሩ፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው ጎርፍ አሁን በደቡባዊ የአገሪቱ ክፍሎች በሰው ሕይወት በእንሰሳትና ማሳ  ላይ ውድመት ማስከተሉን አመልክተዋል።

መንግሥት ዝናቡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በጎርፍ አደጋው እስከ 500 ሺሕ ሕዝብ ሊፈናቀል እንደሚችል መተንበዩንና ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

በጎርፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ዝግጅት እየተደረገ ቢሆንም፣ ጎርፉ የሚያጠቃቸውን አካባቢዎች በሙሉ መተንበይ እንደማይቻል ተናግረዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...