Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባን የቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት መሬት የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት ሚኒስትሩ ገለጹ

የአዲስ አበባን የቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት መሬት የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት ሚኒስትሩ ገለጹ

ቀን:

– ጠፉ ስለሚባሉ የኮንዶሚኒየም ሕንፃዎች አጣርተው ሪፖርት እንዲያደርጉ በፓርላማው ታዘዋል

የአዲስ አበባን የመኖሪያ ቤትና የግንባታ ፍላጎት ለማርካት የመሬት አቅርቦት ችግር ፈተና መሆኑን፣ መፍትሔውም መሬት አልምቶ ማቅረብ ብቻ እንደሆነ የቤቶችና የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ ለፓርላማው ገለጹ፡፡ የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ባለፈው ማክሰኞና ረቡዕ ግንቦት 2 እና 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፓርላማ ሪፖርት ያደረጉት ሚኒስትሩ፣ በአዲስ አበባ የመሬት ፍላጎት ጥያቄን መመለስ እጅግ ፈታኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

‹‹በአዲስ አበባ ለግንባታ የተመቸ አንድም ካሬ ሜትር መሬት ያልተያዘ የለም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ሕገወጥነትን ሥርዓት ስናስይዝ ደግሞ ይህንን መሬት የያዘውም ሰው ባለመብት ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ፈተና እንዴት ነው የሚፈታው የሚለው የመንግሥት የቤት ሥራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም የአርሶ አደሩን ሥጋት በማስወገድ መሬት የማቅረብ ሥራን መንግሥት ማከናወን እንዳለበት በዋነኝነት ጠቅሰዋል፡፡

የአርሶ አደሩን ሥጋት ለመቅረፍም በዋናነት መቀመጥ የሚገባቸው ሁለት መሠረታዊ መፍትሔዎች የካሳ ጉዳይና አርሶ አደሩ መሬቱን የሚለቀው በትክክልም ለልማት ሥራ መሆኑን በማረጋገጥ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በበርካታ አካባቢዎች በልማት ስም አርሶ አደሩ እየተፈናቀለ በመሆኑ፣ ይህንን ለይቶ በትክክል ዕርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ  ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የቤቶችና የከተማ ልማት ሚኒስቴር የካሳ አዋጁን የመከለስ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ለአርሶ አደሩ ጠቃሚ ካሳ ብቻ ከፍሎ ዞር ማለት ሳይሆን አርሶ አደሩ መሬቱን ከለቀቀ በኋላ ቀጣይ ሕይወቱ ከቀድሞ የተሻለ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የተለያዩ ፓኬጆች እየተቀረፁ መሆናቸውን፣ ከእነዚህም መካከል የከተማ ግብርና፣ የጥቃቅንና አነስተኛ፣ የቤቶች ልማትና የመሳሰሉት እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡ ይህ ከሆነ በአጠቃላይ ልማቱ ሳይስተጓጎል መቀጠል እንደሚችል እምነታቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አሁን ላለው የቤቶች ልማት አቅርቦት ፍጥነት መንግሥት የተዘመገበውን ቤት ፈላጊም ሆነ አዲስ የሚመጣውን ማስተናገድ እንደማይችል ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም መሬት ማቅረብና ቤት ፈላጊዎች ቆጥበው የራሳቸውን መኖሪያ ቤት እንዲገነቡ ማድረግ፣ የውጭ ባለሀብቶችና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በቤቶች ልማት እንዲሳተፉ መሬት ማቅረብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ‹‹መንግሥት መሬት በማቅረብ ችግሩን ካልቀረፈ መጠየቅ አለበት፤›› ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ለባለዕድለኞች የተላለፉ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማጣራት በተደረገው ቆጠራም፣ 4,177 ቤቶች በአግባቡ በሕጋዊነት ጥቅም ላይ ሳይውሉ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለተጠቃሚዎች ሳይተላለፉ የቀሩት 3,512 መሆናቸውን፣ በሕገወጥነት የተያዙ 92፣ እንዲሁም ለመንግሥት አመራሮች ተላልፈው አመራሮቹ ለሦስተኛ ወገን ያከራዩዋቸው 286 ቤቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ከክልል የመጡ የፖለቲካ አመራሮችና የሕክምና ባለሙያዎች የተሰጡዋቸውን ቤቶች ለሦስተኛ ወገን ካስለተላፉት መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ‹‹የጠፉ›› የኮንዶሚኒየም ሕንፃዎች አሉ በማለት የሚናፈሱ መረጃዎችን በተመለከተ ምንም ዓይነት መረጃ አላቀረቡም፡፡ ይህም አንዳንድ የፓርላማ አባላትን ያስቆጣ ሲሆን፣ በራሳቸው ለማጣራት በሞከሩበት ወቅትም ለመገንባት ታቅደው ያልተገነቡ ሕንፃዎች መኖራቸውን በመግለጽ ጥርት ያለ ምርመራ ተደርጎ ሪፖርት እንዲደረግላቸው ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡ ፓርላማውም በዚሁ አግባብ ሚኒስትሩን ያዘዘ ሲሆን፣ ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌም በተቋም ደረጃ ማጣራት አድርገው ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...