Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ከተማ መሬት አሰጣጥ ኦዲት ሊደረግ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አሰጣጥ ኦዲት ሊደረግ ነው

ቀን:

ሕግ በጣሱ ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል ተብሏል

የተወሰኑ የመሬት አገልግሎቶች ታግደዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በመሬት ዘርፍ አጠቃላይ ኦዲት አካሂዶ በጥፋተኞች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ፣ የምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ትዕዛዝ እየጠበቀ ነው፡፡

በምክትል ከንቲባው የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ካቢኔ ሪፎርም ያስፈልጋቸዋል ካላቸው ዘርፎች ግንባር ቀደሙ መሬትና መሬት ነክ ዘርፍ ነው፡፡

ይህንን ሪፎርም ለማካሄድ ከሚከናወኑ ሥራዎች መካከል ከዚህ ቀደም ለኢንቨስተሮች በተለይም ለሪል ስቴት፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለመኖሪያ ቤቶችና ለንግድ ሕንፃዎች በሊዝ ጨረታና በድርድር የተሰጡ ቦታዎች ኦዲት ይደረጋሉ ተብሏል፡፡

በኦዲት ወቅት ከሕግና ከመመርያ ውጪ ቦታ አስፋፍተው የያዙ፣ በጥቅም ትስስር በሕገወጥነት ቦታ የያዙ፣ ከግንባታ ፈቃድ ውጪ ግንባታ ያካሄዱና ለዓመታት አጥረው የያዙ አልሚዎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው የአስተዳደሩ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

 ምክትል ከንቲባ ታከለ የመሬት ዘርፍ ሪፎርምና ኦዲት ከመካሄዱ በፊት የተወሰኑ አገልግሎቶች እንዲታገዱ ወስነዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል በቅርቡ የወጣው 30ኛው የመሬት ሊዝ ጨረታ፣ የኢንዱስትሪ አልሚዎች የመሬት ጥያቄ፣ የሠነድ አልባና አግባብ ካለው አካል ሳይፈቅድ በወረራ የተያዙ ቦታዎች መስተንግዶ፣ መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት መስተንግዶ አገልግሎቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በከተማው ታጥረው ለዓመታት በተቀመጡ 186 ሔክታር የመልሶ ማልማት ቦታዎች ላይ፣ አስተዳደሩ ሲከተል የቆየውን አሠራር እንደሚለውጥና ተነሽዎችን ከግምት ያስገባ እንደሚሆን ምክትል ከንቲባ ታከለ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬትና መሬት ነክ ዘርፍ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ኦዲት የተካሄደው ከሰባት ዓመታት በፊት በ2003 ዓ.ም. ነበር፡፡

በወቅቱ የተካሄደው ኦዲት በሁሉም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሳይሆን፣ በተለይ በሪል ስቴት ዘርፍ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ በወቅቱ በነበረው መዋቅር የመሬት ዘርፍ የሚመራው በከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ነበር፡፡ ሥራውንም ሆነ የሚወሰደውን ዕርምጃ የመሩት፣ በቅርቡ የከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት በዚያ ወቅት ግን ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አወቀ ኃይለ ማርያም (ኢንጂነር) ናቸው፡፡

በወቅቱ 105 የሪል ስቴት ኩባንያዎች አግባብ ካለው አካል ሳይፈቀድ ቦታ አስፋፍተው በመያዝ፣ አፓርታማ ለመገንባት በወሰዱት ቦታ ላይ ቪላ ቤቶችን በመገንባት፣ ሕጉ መሬት አይሸጥም አይለወጥም ቢልም ምንም ዓይነት ግንባታ ሳያካሂዱ ለሦስተኛ ወገን በማስተላለፋቸው ዕርምጃ ተወስዶባቸው ነበር፡፡

ጥቂቶች በፍርድ ቤት ሲጠየቁ ሌሎች በአስተዳደራዊ ዕርምጃ ብቻ ታልፈዋል፡፡ የተወሰኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ዕርምጃ ሳይወሰድባቸው ሾልከው ማለፋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በወቅቱ ከሪል ስቴት በመቀጠል ለኢንዱስትሪ ልማት የተሰጡ ቦታዎች ላይ ኦዲት ለማካሄድ ሥራ የተጀመረ ቢሆንም፣ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሥራው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች መልካም አስተዳደር ዕጦት ብቻ ሳይሆን፣ ሙስና የተንሰራፋባቸው መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ይህንን ብልሹ አሠራር እንዲያስተካክሉና መሥሪያ ቤቱንም እንዲመሩ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጂነር) ናቸው፡፡ አቶ ሽመልስ ከሠራተኞች ጋር ከተዋወቁ በኋላ ቀጣዩን ሥራ ለማከናወን ደንብና መመርያዎችን በማጥናት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...