Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መንግሥትን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የሚያማክር ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥትን በአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያማክር ምክር ቤት ሊቋቋም ነው፡፡

በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ሥር ሆኖ እንደሚሠራ የተገለጸው ይህ ምክር ቤት፣ ከተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎችንና የንግድ ሰዎችን ያካተተ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በሒልተን ሆቴል ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽነር አቶ እዮብ ተካልኝ ካደረጉት ገለጻ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በቅርቡ ይፋ የሚደረገው አማካሪ ምክር ቤት በኮሚሽኑ ሥር ይዋቀራል፡፡ ሆኖም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን፣ የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶለትም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሚመክርበት ቋሚ ፕሮግራም እንደሚኖረውና የምክር ቤቱ አባላትም በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡

አማካሪ ምክር ቤቱ በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያከናውናቸው በርካታ ሥራዎች እንደሚኖሩት፣ ያከናውኗቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ ከንግዱ ማኅበረሰብ የሚቀርቡ ሐሳቦችን በማጠናቀርና የመፍትሔ ሐሳቦችን በማመላከት ለፖሊሲ ግብዓት እገዛ ማድረግ ነው፡፡

በተለይ በግሉ ዘርፍ ውስጥ ችግሮች ሲፈጠሩ መፍትሔ በማመንጨት ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ይሠራል ተብሏል፡፡ ለምሳሌ አንድ መደብር ተከፍቶ በሳምንቱ ቢዘጋ ለምን ተዘጋ? ችግሩ ምንድነው? በማለት የችግሩን ምንጭ በማወቅ ለመፍትሔ እንደሚሠራ ተጠቁሟል፡፡ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ባሉበት ከቆሙና ዕድገት ያልተለየባቸው ከሆነ፣ ለምን የሚለውን ጥያቄ ይዞ ሌሎች በንግድ ውስጥ የሚታዩ ችግሮችን በመቃኘት መፍትሔ ለማፈላለግ የሚሠራ ጭምር እንደሚሆን አቶ እዮብ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ችግሮች እየታዩ እንደማይታለፉ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ለምክር ቤቱ መፍትሔ የሚረዱ የውሳኔ ሐሳቦችን ያቀርባል ብለዋል፡፡ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ አሁን አሉ የሚባሉ ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የግሉ ዘርፍ የሚያቀርባቸውን ማናቸውንም ሐሳቦች እንደሚቀበሉ የገለጹት አቶ እዮብ፣ ‹‹ከሰማይ በታች አስፈላጊ የሆኑ ሐሳቦችን በሙሉ እንቀበላለን፡፡ ለአገር ዕድገት እስከጠቀሙ ድረስ ተግባራዊ ይደረጋሉ፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች