Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሁለተኛው ‹‹ናትና›› የጎዳና ላይ ሩጫ በመቀሌ ይካሄዳል

ሁለተኛው ‹‹ናትና›› የጎዳና ላይ ሩጫ በመቀሌ ይካሄዳል

ቀን:

በአትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያምና አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ መሥራችነት የሚሰናዳው ዓመታዊው የጎዳና ላይ ሩጫ ዘንድሮም በርካታ አንጋፋ  አትሌቶችን እንደሚያሳትፍ አዘጋጁ አስታወቀ፡፡ የትግራይ ክልልን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማጎልበት ቀዳሚ ግቡ ባደረገው በዚህ ውድድር፣ ከ15 ሺሕ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

መነሻና መድረሻውን በሮማንት አደባባይ ያደረገው ሁለተኛው የናትና የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ‹‹ወጋገን ናትና የጎዳና ላይ ሩጫ›› የሚል ስያሜን በመያዝ ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ይከናወናል፡፡

ከጅምሩ ሲቋቋም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዞኖች ውስጥ በየሁለት ወሩ ለአንድ ዓመት ያህል ውድድር ካካሄደ በኃላ፣ የከተማዋን ኅብረተስበ በማካትት ፍፃሜውን በመቀሌ እንደሚያከናውን የናትና ስፖርት ኤቨንትስ ቦርድ ሰብሳቢ ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አትሌት ገብረ እግዚአብሔር፣ ከውድድሩ በሚገኘው የቲሸርት ሽያጭና የስፖንሰርሺፕ ገቢ ሦስት የስፖርት ማዕከላትን በማስገንባት ለክልሉ ወጣቶች ለማስረከብ ማቀዱን ተናግረሯል፡፡

ከተቋቋመ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው ናትና ዓመታዊ የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡ በዚህም መሠረት አንደኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ አትሌት ሃምሳ ሺሕ ብር፣ ለሁለተኛ ሠላሳ ሺሕ፣ ለሦስተኛ አሸናፊ ደግሞ የሃያ ሺሕ ብር ሽልማት መዘጋጀቱን አትሌት ገብረ እግዚአብሔር አስታውቋል፡፡ ከገንዘቡ ሽልማት ባሻገር ለአትሌቶች የውድድር አማራጭ ማብዛት ሌላው ናትና ውድድር የሚያስገኘው ዕድል ሲሆን፣ ሁሉም ክለቦችና የግል አትሌቶች እንዲሳተፉ ጥሪው ቀርቦላቸዋል ተብሏል፡፡

ዓመታዊ ውድድሮች በየክልሎች መዘውተራቸው፣ ማኅብረሰቡን ከማቀራረብ ጎን ለጎን ሕዝቡን ወደ ስፖርቱ በማምጣት የበለጠ እንዲሳተፍ ለማድረግ እንደሚያስችል አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ የማኅበረሰቡን ትስስር በማጠናከርም የክልሉን ስፖርት መደገፍ የውድድሩ ዓላማ እንደሆነም ገልጿል፡፡

ውድድሮቹ በየዞኑ ሲከናወኑም የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን ለማስተዋወቅና የሌላው አካባቢ ተወላጅ ስለክልሎች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ይረዳል ተብሏል፡፡ ከአዲስ አበባ 780 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መቀሌ ከተማ የሚሰናዳው የጎዳና ላይ ሩጫ ላይ ከ15 ሺሕ በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ፡፡

እንደ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር አስተየየት ከሆነ፣ ውድድሩን ዓለም አቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ታዋቂ የውጭ አትሌቶችንም በመጋበዝ ውድድሩን የማስፋት ዕቅድ እንዳለ አብራርቷል፡፡ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት አጋር ድርጅቶች አለመኖራቸውና የግንዛቤ ችግር ውድድሩን እንደሚፈለገው ለማስፋፋት እንቅፋት እንደሆነ የናትና መሥራችና ቦርድ ሰብሳቢ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ጠቅሷል፡፡ ማኅበረሰቡ ከስፖርቱ ጋር ያለው ቁርኝት ቀዝቃዛ መሆንም ሌላኛው ችግር እንደሆነም ተነስቷል፡፡

ናትና በትግራይ ክልል ብቻም ሳይሆን፣ በሌሎች አካባቢዎችም የሚከናወኑ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ዓላማ አንግቦ የተነሳ ተቋም እንደሆነም ተብራርቷል፡፡ ከአዋቂዎቹ ውድድር ባሻገር 1,500 ሕፃናትን የሚያሳትፍ መሰናዶም በውድድሩ ተካቷል፡፡

ከዚህ ቀደም በአትሌት ገብረ እግዚአብሔር ሲሰናዳ የሚታወቀውና ዓመታዊው የኢትዮትሬይል የተራራ ላይ ሩጫ በወቅታዊው የክልሎች የፀጥታ ችግርና አለመረጋጋት ምክንያት ቢቋረጥም በቅርቡ ሊካሄድ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ከአዘጋጁ ለመረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...