Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓቃቤ ሕግ በቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ለመርማሪዎች መለሰ

ዓቃቤ ሕግ በቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ ለመርማሪዎች መለሰ

ቀን:

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን በሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቤ ሕግ ያስረከበ ቢሆንም፣ ዓቃቤ ሕግም መዝገቡን መርምሮ ለድጋሚ ምርመራ ለመርማሪ ቡድኑ እንደመለሰለት ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

 መርማሪ ቡድኑ ምርመራውን አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ ማስረከቡን መግለጹንና ዓቃቤ ሕግም በማረጋገጡ፣ ለሰኞ ሐነሴ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ የሰባት ቀናት የክስ መመሥረቻ ለሁለተኛ ጊዜ ተፈቅዶለት ነበር፡፡

ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ግን ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ መሥርቶ ሳይሆን፣ መርማሪ ቡድኑ የሰጠውን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ለመርማሪ ቡድኑ እንደመለሰለት ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት ነው፡፡ መዝገቡን ለፍርድ ቤቱ ለምን እንደመለሰ ሲያብራራ፣ መርማሪ ቡድኑ የምርመራ መዝገቡን ያስረከበው በቦምብ ፍንዳታው ጉዳት ከደረሰባቸው ተጎጂዎች ውስጥ የ40 ሰዎችን ቃል ብቻ ተቀብሎ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ነገር ግን ተጎጂዎች ከ100 በላይ በመሆናቸውና የሁሉም ቃል አስፈላጊ በመሆኑ፣ የቀሪዎቹን ቃል ተቀብሎ እንዲያስረክበው መዝገቡን እንደመለሰለት ገልጿል፡፡ በተጨማሪም ቦምብ በማቀበል የተጠረጠረው አቶ ብርሃኑ ጃፋርና ቦምቡን ወርውሮ ሊያመልጥ ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ጥላሁን ጌታቸው፣ ከሰኔ 12 እስከ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ያደረጉትን የስልክ ንግግር ከኢትዮ ቴሌኮም አስወጥቶ የምርመራ መዝገቡ አካል ማድረግ ስለሚቀረው አጠናቆ እንዲያስረከበው ለመርማሪ ቡድኑ መዝገቡን መመለሱን ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ችሎት አስረድቷል፡፡

መርማሪ ቡድኑም መዝገቡ እንደተመለሰለት በማረጋገጥ፣ ቀሩ የተባሉትን የምርመራ ሒደቶች አጠናቆ ለማስረከብ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሕክምና እንደማያገኙና ቤተሰብ እንደማይጠይቃቸው፣ እንዲሁም መርማሪ ቡድኑና ዓቃቤ ሕግ እርስ በርስ አንዱ በአንዱ እያሰባሰቡ ምርመራቸውን ሊያጠናቅቁ ባለመቻላቸው፣ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲያሰናብታቸው ወይም ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል፡፡ የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን በማለፍ መርማሪ ቡድኑ ሰባት ቀናት ውስጥ ምርመራውን ጨርሶ እንዲያስረክብ ትዕዛዝ በመስጠት፣ ለነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመደገፍ በመስቀል አደባባይ በወጣው ሕዝብ ላይ ቦምብ ተወርውሮ፣ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...