Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው

ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው

ቀን:

ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ላይ፣ ክስ እንዲያቀርብና ውጤቱንም እንዲገልጽ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ትዕዛዙን የሰጠው፣ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪ አቶ ቢኒያም ተወልደና አቶ ሰላም ይሁን አደፍርስ ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናቆ፣ ለዓቃቤ ሕግ እንዲያስረክብ ተሰጥቶ የነበረውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ ምክንያት ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ ከፖሊስ የምርመራ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ አለመሰጠቱንና የተጻፈ ደብዳቤም እንደሌለ ገልጿል፡፡ ድርጊቱ ተገቢ አለመሆኑንና ለወደፊቱም መደገም እንደሌለበት መርማሪ ቡድኑን በችሎት አስጠንቅቋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ በተፈቀደለት አሥራ አንድ ቀናት ውስጥ ምንም ሳይሠራ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ተገቢ አለመሆኑን ጠቁሞ፣ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ አሳልፎ እንዲሰጥ በችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አቶ ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ባቀረቡት ክርክር እንደተናገሩት፣ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በፍርድ ቤት የቀረበባቸው የተጠረጠሩት ወንጀል ሥልጣንን ያላግባብ መገልገልና ሀብት ማከማቸት ነው፡፡ ይኼንን ለማጣራት ደግሞ ለመርማሪ ፖሊስ ከበቂ በላይ ጊዜ ስለተሰጠው ምርመራውን ማጠናቀቁን ፍርድ ቤቱ ተገንዝቦ፣ ለዓቃቤ ሕግ እንዲያስረክብ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ትዕዛዙን አለማክበሩን አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ለመርማሪ ቡድኑ የተሰጠው ጊዜ ከበቂ በላይ ስለሆነና የሚቀረው ሥራ የኦዲት ሪፖርት በመሆኑ፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ሰላም ይሁንም ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት፣ ከተያዙ ጀምሮ ቃል አልሰጡም፡፡ ይኼ የሚያሳየው ምንም ዓይነት ወንጀል እንደሌለባቸውና ወንጀልም እንዳልተፈጸመ ስለሆነ፣ ነፃ ሆነው የመገመት መብታቸው ተከብሮ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ደግሞ የዋስትና  መብት ጥያቄውን ተቃውሞ ተከራክሯል፡፡ ፍርድ ቤቱም የዋስትና ጥያቄውን በማለፍ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ትዕዛዝ ለዓቃቤ ሕግና ለመርማሪ ፖሊስ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...