Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትታዳጊዎች የሚመዘኑበት አገር አቀፍ ውድድር እየተካሄደ ነው

ታዳጊዎች የሚመዘኑበት አገር አቀፍ ውድድር እየተካሄደ ነው

ቀን:

የትግራይና የኢትዮ ሱማሌ ተወካዮች አልተሳተፉም

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚያዘጋጁት አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች የሚመዘኑበት ስፖርታዊ ውድድር በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ውድድሩ ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ.ም.  ፍጻሜውን እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት በአዳማ ከነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ በሰነበተውና በስድስተኛው አገር አቀፍ የታዳጊዎች ምዘና ውድድር በአጠቃላይ 2,097 አትሌቶች ሲሳተፉ 852ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከሆነ፣ 361 አትሌቶችም በፓራሊምፒክ እየተሳተፉ ነው፡፡ ይህም ሆኖ በውድድሩ ከትግራይና ከኢትዮጵያ ሱማሌ በስተቀር ሌሎቹ ክልሎች ተሟልተው መቅረባቸው ታውቋል፡፡

የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በበላይነት የሚመራው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር፣ የዘንድሮው ለስድስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ከመሆኑ በሻገር፣ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ውድድሮች ከተሳተፉ አትሌቶች ውስጥ ምን ያህሉ በሚፈለገው መጠን አገልግሎት ሰጥተዋል? የሚለው በውል ባይታወቅም፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለሁሉም ስፖርቶች ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖ ለሚገኘው ታዳጊዎችን የማፍራት ችግር እንዲህ ያለው ውድድር መዘጋጀቱን በመፍትሔነት የሚመለከቱት ጥቂቶች አይደሉም፡፡

የምዘና ውድድሩን ጠቀሜታ አስመልክቶ ተሳታፊዎች ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲናገሩ እንደተደመጠው ከሆነ፣ ‹‹ዝግጅቱን በበላይነት የሚመራው ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴርም ሆነ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ክልሎች ለዚህ መሰሉ ሻምፒዮና ከመቅረባቸው በፊት በውድድር ዓመቱ የሚከውኗቸው እንቅስቃሴዎች ምን እንደሚመስሉ የሚከታተሉበት የጊዜ ሰሌዳ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በሁሉም ክልሎች ሊባል በሚችል ደረጃ የዘንደሮውን ጨምሮ ዓመታዊ ሻምፒዮናው ሲቃረብ ካልሆነ በቀር ትክክለኛውን ሥራ ሠርቶ የሚቀርብ ክልል የለም፤›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔውን በሚያደርግበት ወቅት በሪፖርቱ እንዳመለከተው፣ ለሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች በየዓመቱ የገንዘብና የትጥቅ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ይሁንና  የገንዘቡም ሆነ የትጥቅ ድጋፉ በትክክል ለአትሌቶቹ መድረስ አለመድረሱ ስለማይገመገም፣ በአብዛኛው የክልል ካቢኔ አባላት እንደሚቀራመቱት ሲገለጽ ተደምጧል፡፡ በአዳማው የታዳጊዎች ምዘና ውድድር ላይ ከታደሙት መካከል ከተስተጋቡ ቅሬታዎች የአንዳንዶቹ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ነበሩ፡፡

ሌላው በክልሎቹ እንደ ክፍተት ሲነሳ የተደመጠው በአዳማ ሲካሄድ በሰነበተው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር፣ በ17 የስፖርት ዓይነቶች ተደልድሎ ቢሆንም፣ እግር ኳስና አትሌቲክስን ጨምሮ በየስፖርት ዓይነቱ የሚመለከታቸው የብሔራዊ ፌዴሬሽን ተወካዮች አለመገኘታቸውን ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ውድድሩን በበላይነት የሚመራው አካል የዘንድሮውን ጨምሮ እስከ ዛሬ የተከናወኑ ውድድሮችን በባለቤትነት እግር ኳሱን ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ አትሌቲክሱንና ሌሎች ስፖርቶችንም በተመሳሳይ አኳኋን ለሚመለከታቸው ፌዴሬሽኖች ሚናውን በመተው የሚኒስቴሩ ድርሻ ድጋፍና ክትትል ላይ የተመረኮዘ መሆን ሲገባው አወዳዳሪ አካል ሆኖ መዝለቁ ችግር እንደሆነ  ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባቱ ውጥን

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በሦስት ዙር ተካሄዶ በነበረው ጦርነት ምክንያት...

በርካታ ሰዎችን እያጠቁ የሚገኙት የሐሩራማ አካባቢ በሽታዎች

ትኩረት የሚሹ የትሮፒካል /ሐሩራማ በሽታዎች በአብዛኛው ተላላፊ ሲሆኑ፣ በዓይን...

ስለአገር ኢኮኖሚ ማሰብ የነበረባቸው ጭንቅላቶች በማያባሩ ግጭቶች ተነጥቀዋል!

አገራችን ኢትዮጵያ ውጪያዊና ውስጣዊ ፈተናዎቿ መብዛት ብዙ ዋጋ እያስከፈላት...