Friday, January 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋልያዎቹ ከወዳጅነት ጨዋታ ድርቅ አልተላቀቁም

ዋልያዎቹ ከወዳጅነት ጨዋታ ድርቅ አልተላቀቁም

ቀን:

ከሴራሊዮን ጋር የምድብ ማጣሪያ ውድድር ይጠብቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ከሾመና 34 ዕጩ ተጨዋቾችን መልምሎ በሐዋሳ ከተማ ልምምድ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይሁንና የዋሊያዎቹን አቋም የሚለካ፣ የሚገኙበትን የዝግጅት ጥንካሬና ብቃት ለመፈተሽ የሚያስችል የወዳጅነት ጨዋታ አልተደረገም፡፡

ኤርትራን ጨምሮ ሦስት አገሮች ለወዳጅነቱ ጨዋታ ጥሪ ተደርጎላቸው ምላሽ አለመስጠታቸውም በፌዴሬሽኑ በኩል እየተነገረ ነው፡፡ የቡድኑ የሥልጠና ዝግጅት በቀን ሁለት ጊዜ እየተካሄደ እንደሚገኝ ሲታወቅ፣ ጳጉሜን ላይ ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር በሐዋሳ እንደሚጫወት የወጣው የውድድር መርሐ ግብር ያሳያል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2019 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ውድድር ዋልያዎቹ እንደሚሳተፉ ቢታወቅም፣ ለዚህ ውድድር የሚያበቃ የአቋም መፈተሻ የወዳጅነት ግጥሚያ መካሄድ አለመካሄዱ ግን አጠራጣሪ እየሆነ መጥቷል፡፡

የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታው ፈቃደኛ እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የሩዋንዳና የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድኖችም ጥያቄው ቀርቦላቸው፣ እስካሁን ምላሽ  እንዳልሰጡ ሪፖርተር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ የወዳጅነት ግጥሚያ ለማድረግ የተጠየቁት ቡድኖች ምላሻቸውን አላሳወቁም፡፡ ጥያቄው ከቀረበላቸው ሁለት ሳምንት በላይ ማለፉም ተነግሯል፡፡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ ዋና አሠልጣኙ የዋሊያዎቹን ኃላፊነት በተረከቡ ማግሥት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቡድናቸው የተሟላ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሊኖረው እንደሚገባና ወቅታዊ መረጃዎች ለሚመለከታቸው ሁሉ ተደራሽ እንደሚደረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ እንዲሁ በፊናቸው የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ከሚያደርገው ጥረት ይልቅ፣ በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ሰንጠረዥ ዕውቅና  የተሰጣቸውን የወዳጅነት ጨዋታዎች ቢጠቀምባቸው አቋሙን ለመፈተሽ ተመራጭ እንደሆነ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ይህን ዕድል መጠቀሙ ‹‹ምላሽ አልሰጡም፤ እየተጠበቁ ነው፤›› ከሚሉ ስሞታዎች ይገላግለው እንደነበር አስተያየት ሰጪዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በፊፋ የወዳጅነት ጨዋታዎች የተመዘገቡ መርሐ ግብሮች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአቋም መፈተሻነቱ ባሻገር፣ ዕውቅና የሚያስገኙና በወዳጅነት ጨዋታዎች የሚመዘገቡ ውጤቶች የአገሪቱን ደረጃና ነጥብ የሚያጎለብቱበት ሰፊ ዕድል እንዳላቸው አስተያየየት ሰጪዎቹ ያብራራሉ፡፡ ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ አካሄድ ራሱን ለመገምገምና ለማዘጋጀት እያቅማማ እንደሚገኝ እየታየ ነው፡፡

በሐዋሳ ከሁለት ሳምታት በላይ በልልምድ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ በዝምታ ሥራው ላይ ብቻ ያተኮረ ቢመስልም፣ በጳጉሜን ለሚያካሂደው የአኅጉራዊው የማጣሪያ ውድድር እስካሁን የወዳጅነት ግጥሚያ አላደረገም፡፡ ከዚህ ቀደም ቡድኑ በምድብ ማጣሪያው የመጀመርያውን ጨዋታ ከጋና አቻው ጋር በማድረግ ከሜዳው ውጪ ተጫውቶ በ5 ለ0 ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፎ መመለሱ አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...