Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየልብ ሕክምና ተደራሽነት

የልብ ሕክምና ተደራሽነት

ቀን:

ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ሳቢያ በየዓመቱ ከሚከሰቱት 34 በመቶ ያህሉ ሞቶች መካከል ቀዳሚውን ወይም 15 በመቶ ያህሉን ድርሻ የያዘው የልብ በሽታ ነው፡፡ ከዚህም ሌላ አደጋዎች ዘጠኝ በመቶ፣ ካንሰርና የጉሮሮ በሽታዎች እያንዳንዳቸው አራት በመቶ፣ የደም ግፊት ሁለት በመቶ ድርሻ እንደሚጋሩ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያመለክታል፡፡

ከእዚህም በሽታዎች መካከል በተለይ የልብ በሽታ ምልክቶች በደረት መካከል፣ በክንዶች፣ በግራ ትከሻ ዙሪያ፣ በክርኖች፣ በመንጋጋና በጀርባ አካባቢዎች ሕመምና አለመመቸት ስሜቶች ሲሆኑ፣ የመተንፈስ ችግር ወይም የትንፋሽ እጥረት፣ ትውከትና መገርጣት ከምልክቶቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡  

የልብ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከልም ሆነ ለመቆጣጠር ኅብረተሰቡን ለልብ በሽታ ከሚያጋልጡ አደገኛና ጎጂ ልማዶች ራሱን እንዲጠብቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት ግድ ይላል፡፡

ለልብ በሽታ መንስዔ ናቸው የተባሉትም አጉል ልማዶች ትምባሆ ማጨስ፣ አልኮል ማብዛት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓትን አለማዘውተር መሆናቸውን ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡  

ሕክምናውን ተደራሽ ከማድረግ አኳያም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በጤና ተቋማት ደረጃ የልብ ሕክምና ማዕከላትን መገንባትና ቀደም ሲል የተገነቡትንም ማሻሻልና ማስፋፋት አስፈላጊ ነው፡፡

በአለርት ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ300 በላይ አልጋዎች የሚይዝ፣ ዘመናዊ የሕፃናት የልብ ሕክምና ማዕከል በሚቀጥለው ዓመት እንደሚገነባ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የክሊኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር ዶ/ር ይበልጣል መኮንን ተናግረዋል፡፡

ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሆስፒታሉ የሚገነባው በ1.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ሲሆን፣ ይህም የሚሸፈነው በመንግሥት በጀት ነው፡፡

ከዚህም ሌላ ቀደም ሲል የተቋቋመው የጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል የሕፃናትና የአዋቂዎች የልብ ሕክምና ማዕከልን በ80 ሚሊዮን ዮሮ ለማስፋፋት የሚያስችል ስምምነት በሆላንድና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል ስምምነት መፈረሙን አስረድተዋል፡፡

ከዶ/ር ይበልጣል ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በተለያዩ ቦታዎች ቀደም ሲል ከተቋቋሙት የልብ ሕክምና ማዕከላት ውስጥ የአይደር ሆስፒታል ማዕከል አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ደግሞ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የልብ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው የማሽን ተከላ ሥራም ተጠናቋል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የልብ ሕክምና ማዕከል ደግሞ በግንባታ ላይ ነው፡፡

በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው ኼው ባለስድስት ፎቅ ሕንፃ ግንባታ ሲጠናቀቅ የልብ ሕክምና ለኅብረተሰቡ ተደራሽ የመሆኑን ሥራ በይበልጥ ያጠነክረዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የጤና ተቋም መሥራት ማለት ሕንፃውን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ በሰው ኃይል፣ አስፈላጊ በሆኑ የመገልገያ መሣሪያዎች ማሟላትና የአሠራር ሥርዓቶችን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ዕውን መሆን አስፈላጊው እንቅስቃሴ ሁሉ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የአሠራር ሥርዓት የመዘርጋቱ፣ በሰው ኃይልና የመገልገያ መሣሪያዎች የማደራጀቱ ተግባር ሕክምናና ምርመራው በተሻለ መንገድ እንዲከናወኑ የሚያደርጉ መሆናቸውን ነው ዶ/ር ይበልጣል የተናገሩት፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...