Sunday, April 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የጉበት ካንሰር የሚያመጣ የአፍላቶክሲን ክምችት በቅባት እህሎች ውስጥ መገኘቱን የባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አረጋገጠ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ለውዝን ጨምሮ በቆሎና ማሽላ ጥናት እየተካሄደባቸው ነው

የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውንና በሻጋታ ምክንያት የሚከሰተውን አፍላቶክሲን ማጥናት ከጀመረ በኋላ፣ በተለይ በለውዝ ቅባት እህል ላይ እስከ 80 በመቶ የሚጠጋ የአፍላቶክሲን ክምችት መገኘቱን አረጋገጠ፡፡ ለጉበት ካንሰር መፈጠር መንስዔ መሆኑ ታውቋል፡፡

በኢንስቲትዩቱ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት የአፍላቶክሲን ክምችትን በማጥናት፣ መፍትሔውን ለማመላከት ሳይንሳዊ ምርምር መደረግ ከጀመረ ሦስት ወራት አስቆጥሯል፡፡ ይሁንና በጥናቱ መነሻ ወቅት በተደረጉ የመስክና የላቦራቶሪ ፍተሻዎች ማረጋገጥ እንደተቻለው፣ በለውዝ አምራችነታቸው ከሚታወቁት አካባቢዎች መካከል በምዕራብና በምሥራቅ ሐረርጌ ሦስት ወረዳዎች ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የለውዝ ምርት በአፍላቶክሲን አምጪ ሻጋታ ተጠቅተዋል፡፡

የጥናት ፕሮጀክቱን የሚመሩትና በኢንስቲትዩቱ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ፍሬው ታፈሰ (ዶ/ር) ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ በጉርሱም፣ በባቢሌና በዶሎለቡ ወረዳዎችና በወረዳዎቹ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ከእያንዳንዱ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ለናሙና ተመርጠው በተደረገ የመጀመርያ ደረጃ ጥናት መሠረት፣ በለውዝ ምርት ውስጥ አፍላቶክሲን ተገኝቷል፡፡ ናሙናው አፈርን ጨምሮ ከገበሬዎች፣ እንዲሁም ለገበያ ለማቅረብ ከተዘጋጀና ለልዩ ልዩ የምግብ ማዘጋጃ ይሆን ዘንድ ለፋብሪካዎች እንዲቀርብ በመጋዘን ተከማችቶ የነበረ ለውዝ ላይ በተደረገ ምልከታ በግልጽ የሚታይ ሻጋታ ተገኝቷል፡፡

እንደ እሳቸው ገለጻ ከሆነ አፍላቶክሲን ቢ የተሰኘውና ለጉበት ካንሰር መፈጠር መንስዔ የሆነው ሻጋታ በኢትዮጵያ የቅባት እህል ምርቶች ላይ በመታየቱ፣ ይኼንን ችግር የሚቀርፍ ጥናት በማካሄድ መፍትሔ ለማፈላለግ የሚያስችል ሳይንሳዊ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡ የባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባገኘው የአራት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አማካይነት ጥናቱን በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም በለውዝ፣ በሰሊጥ፣ በበቆሎና በማሽላ ምርቶች ላይ ያተኮረ ምርምር በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተመራማሪው ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በቅርቡ ለመገናኛ ብዙኃን ያሠራጨው ጽሑፍ እንደሚያትተው፣ በኢትዮጵያ የችግሩ አሳሳቢነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ እየታወቀ ቢመጣም፣ 1999 .. ጀምሮ በተካሄዱ የምርምር በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች ውስጥ  በተለይም በጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስና ማሽላ ላይ በተደረገ ዳሰሳ ጥናት አፍላቶክሲንን ጨምሮ በተለያዩ የማይኮቶክሲን ዓይነቶች መበከላቸው ታውቋል።

ኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ታዳጊ አገሮች ሁሉ በምግብ እህሎች ውስጥ የሚገኘው የአፍላቶክሲን መጠን ከፍ እንደሚል ይገመታል፡፡ በቅርቡ ወደ ውጭ ተልከው ከሚፈቀደው በላይ የአፍላቶክሲን መጠን ተገኝቶባቸው የተመለሱ የበርበሬ ምርቶችም ይኼንኑ ያረጋግጣሉ፡፡ ከርበሬ በተጨማሪ የለውዝ ምርት ወደ አውሮፓ እንዳይገባ እየተከለተከለ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ማይኮቶክሲኖች የፈንገሶች (ሻጋታዎች) መርዛማ የሥነ ይወታዊ ሒደት ውጤት ሆኑ መርዛማ ኬሚካሎች ጥቅል ሞች ናቸው፡፡ ነዚህም ማይኮቶክሲኖች መካከል አደገኛና ካንሰር አምጭ የሆኑት አፍላቶክሲኖች ዋነኞቹ ናቸው። የአፍላቶክሲን ብክለት በዓለም አቀፍ የምግብና የመኖ ንነት ጋት መሆን የጀመረው ልሳ መታት በፊት ... 1960 በእንግሊዝ 100,000 የዶሮ ዝርያዎች (ተርኪ) ሞት ምክንያት መሆኑ ከታወቀ ወዲህ ስለመሆኑ የኢንስቲትዩቱ መረጃ ይጠቁማል፡፡

ዋና ዋና የአፍላቶክሲን ይነቶች አራት ናቸው፡፡ አፍላቶክሲን አንድ፣ አፍላቶክሲን ሁለት፣ አፍላቶክሲን አንድ፣ አፍላቶክሲን ሁለት ይባላሉ፡፡ እነዚህ ሻጋታ በብዛት በአፈር ውስጥ በመገኘታቸው በቀላሉ ሰብሎችን ሊበክሉ ይችላሉ። ከፍተኛ የሆነ የአየርና የአፈር ሙቀት ከፍተኛ የሆነ እርጥበት አዘል አየር ንብረት ሃማነትና በእርሻ ማሳ ላይ የሚኖር ከፍተኛ የው እጥረት ደግሞ ሰብሎች በእርሻ ላይ እያሉ በአፍላቶክሲን ብክለት እንዲጋለጡ ያደርጋል። እነዚህ በተጨማሪ ወቅቱን ባልጠበቀ የምርት አሰባሰብ ሒደት በአግባቡ ሳይደርቁ በሚከማቹ ሰብሎች ላይ ያላግባብ በተከማቹና በማጓጓዝ ሆነ በምርት ደት ወቅት በሚፈጠር ከፍተኛ ሙቀትና መታመቅ ምክንያት ፈንገሶቹ በፍጥነት ለመራባትና አፍላቶክሲን ለማመንጨት ምቹ ሁኔታ ይፈርላቸዋል።

በመሆኑም እነዚህ ሰብሎች ለምግብነትም ሆነ ለእንስሳት መኖነት በመዋላቸው ሳቢያ በምግብ ሰንሰለት ውስጥ የአፍላቶክሲን ብክለት ይፈጠራል፡፡ በአፍላቶክሲንና በአፍላቶክሲን አመንጭ በሆኑ ሻጋታ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ከሆኑት የግብርና ውጤቶች መካከል ካሳ በርበሬ፣ ቦቆሎ፣ ጥጥ፣ ለውዝ፣ ሩዝ፣ ሰሊጥ፣ ማሽላ፣ ሱፍ፣ ስንዴና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞችም ይገኙባቸዋል። የእነዚህን ጉዳት ለመቀነስና ለመከላከል ኢንስቲትዩቱ ተፈጥሯዊ የሥነ ሕይወታዊ መለካከያ ዘዴዎች ለመተግበር ጥናት እያካሄደ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ከምርምር ውጤቱ ባሻገር ለአርሶ አደሮችና ለነጋዴዎች፣ እንዲሁም ለምግብ አምራቾች አፍላቶክሲን በኢኮኖሚው ላይ ብቻም ሳይሆን፣ በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት የሚያሳዩ የማስተማር ሥራዎችን በማከናወን ጉዳቱን ለመከላከል እንዳቀደም ፍሬው (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች