‹‹ለስፖርታችን ደህና ጊዜ ይምጣለት! በጋራ ለአገራችን፣ ለሰንደቅ ዓላማችን፣ ለብሔራዊ መዝሙራችን ተዘጋጅተን እንሥራ፡፡ በጋራ እንጣር፡፡ ሐቀኝነት ይኑር፤ ወገናዊነት፣ አድሏዊነት፣ ጠባብነት ይቅር፡፡ የስፖርት መርሑ ይኼ ነው፡፡ ስፖርት በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በቀለም አይከፈልም፡፡ ይኼንን መርሕ አድርገን በዚህ ከሠራን ምናልባት የሸሸን ውጤት ይመጣል ብዬ አምናለሁ፤ ምኞቴም ነው፡፡››
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ፣ ከአራት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሪፖርተር የተናገሩት፡፡