Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሜቴክ በህዳሴ ግድብ የተሰጠው ኮንትራት አለመቋረጡ ተገለጸ

ሜቴክ በህዳሴ ግድብ የተሰጠው ኮንትራት አለመቋረጡ ተገለጸ

ቀን:

‹‹ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች የሜቴክን የሥራ ድርሻ በሰብ ኮንትራት እንዲወስዱ ነው የተደረገው›› የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተሰጠው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ኮንትራት እስካሁን አለመቋረጡን፣ የፕሮጀክቱ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኤፍሬም ወልደኪዳን (ኢንጂነር) ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በተለያዩ መንገዶች እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የተሳሳተ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን የገለጹት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ልምድ ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች የንዑስ ተቋራጭነት ውሎችን ከሜቴክ ጋር በመዋዋል በርካታ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እንዲያከናውኑ መደረጋቸው አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የፕሮጀክቱ ጽሕፈት ቤት የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በተመለከተ ስምምነት ያለው ከብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር ስለሆነ፣ አሁንም ይኼንን ውል በተመለከተ የተለወጠ ነገር አለመኖሩን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን በተመለከተ ኮንትራክተሩ ሜቴክ በአመዛኙ የውጭ ኩባንያዎችን በንዑስ ተቋራጭነት ሲያሠራ እንደነበር ያስታወሱት ኃላፊው፣ የዚህ ምክንያቱም ሜቴክ በዘርፉ ልምድ የሌለው ስለሆነ የተከተለው አሠራር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ንዑስ ኮንትራት የተሰጣቸው እነዚህ የውጭ ኩባንያዎች ለኤሌክትሮ
ሜካኒካል ሥራዎች የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችን በአገር ውስጥ በማምረት እንዲሁም ከውጭ በማስገባት ለሜቴክ ያቀርቡ እንደነበር፣ የተከላ ሥራዎች ግን በሜቴክ ሲከናወኑ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ ሜቴክ የተከተለው ይህ አሠራር ሥራዎችን እያጓተተ በመሆኑ በንዑስ ኮንትራክርነት ውል የፈጸሙት ኩባንያዎች፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን ከማምረት አንስቶ እስከ መገጣጠም ኃላፊነት እንዲወስዱ በቅርቡ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ ሆኖም ሜቴክ በንዑስ ኮንትራክተርነት የሚሠሩት ኩባንያዎችን ሥራ መቆጣጠርና አነስተኛ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን እንደሚሠራ ታውቋል፡፡

አልምስቶን የተባለው የፈረንሣይ ኩባንያ ከሜቴክ ጋር ውል ከፈጸሙት ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ይኼንን ኩባንያ የአሜሪካው ጄኔራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጠቅልሎ በመግዛቱ፣ በህዳሴው ግድብም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን ኃላፊነት በንዑስ ተቋራጭነት ይዞ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ፎይት ኃይድሮ የተባለ የጀርመን ኩባንያም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎችን ከሜቴክ በንዑስ ተቋራጭነት መውሰዱን ገልጸዋል፡፡

‹‹ኮንትራትን ማቋረጥም ሆነ አዲስ ውል መዋዋል ቀላል ተግባር አይደለም፡፡ እስካሁንም ሜቴክ ዋና ኮንትራክተር ነው፤›› ሲሉ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የሜቴክ የግድቡን ግንባታ ማጓተቱን ተናግረዋል፡፡ ሜቴክ ፕሮጀክቱን በማጓተቱም የግንባታ ኮንትራክተሩ ሳሊኒ ኩባንያ ክፍያ እየጠየቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...