Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኮፓ ኮካ-ኮላ የታዳጊዎች ሻምፒዮና በዝዋይ ይጠናቀቃል

የኮፓ ኮካ-ኮላ የታዳጊዎች ሻምፒዮና በዝዋይ ይጠናቀቃል

ቀን:

በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በሁለቱም ፆታ ከ17 ዓመት በታች የዕድሜ ክልል ተደልድሎ ሲካሔድ የሰነበተው የኮፓ ኮካ ኮላ ሻምፒዮና የመዝጊያ ውድድሩን በዝዋይ እንደሚያካሂድ ታወቀ፡፡

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሲያከናውናቸው የሰነበቱትን ውድድሮች ማጠናቀቂያ ዝዋይ ላይ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል፡፡ በ2010 ዓ.ም. መርሐ ግብር የታዳጊዎች ሻምፒዮና በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በጋምቤላ፣ በሐረርና በድሬዳዋና በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉቱም ፆታዎች ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የሻምፒዮናውን ማጠናቀቂያ በዝዋይ ለማድረግ በድሬዳዋ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባና ጋምቤላን ጨምሮ በሴት ዘጠኝ እንዲሁም በወንድ ዘጠኝ፣ በድምሩ 18 ቡድኖች በኮፓ ኮላ ውድድር ይሳተፋሉ፡፡

ኮፓ ኮካ በየዓመቱ በሚያከናውናቸው ውድድሮች አማካይነት በርካታ ታዳጊዎችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አካዴሚ ማብቃት ችሏል፡፡ ባለፈው ዓመት ከ50 በላይ ታዳጊዎችን ለአካዴሚው በማስመረጥ የአራት ዓመታት ስፖርታዊ ቆይታ በማዕከሉ እንዲኖራቸው ዕድሉን አመቻችቶላቸዋል፡፡ የኮካ ኮላ ቅርንጫፍ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ት ትዕግሥት ጌቱ እንደገለጸችው፣ በየዓመቱ በሚደረገው ሻምፒዮና ሒደት ኩባንያው በየጊዜው እያደገ መምጣቱና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የመሠረተው ግንኙነትም በየጊዜው እያደገ መምጣቱን አስታውቃለች፡፡

ከዚህም ባሻገር ዓመታዊው ውድድር ለታዳጊዎቹ ስፖርተኞች በራስ መተማመናቸው እንዲጎለብት ከማገዝ አልፎ ለብሔራዊ ቡድኖችና ለክለቦች አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችሉበትን ዕድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርግላቸዋል ብላለች፡፡

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለታዳጊዎች የተሳትፎ ዕድል የሚሰጠው የኮካ ኮላ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር፣ በእግር ኳስ መስክ ተተኪዎችን ለማፍራት ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚታወቁ ክለቦች፣ ለዋናው ቡድናቸው የሚያገለግሉ ተተኪዎችን ለመመልመል የኮፓ ኮካ ኮላ ውድድሮችን ምርጫቸው ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡

ከክለብ አልፈው ለብሔራዊ ቡድን ጭምር መሳተፍ የቻሉ ሴት ተጫዋቾችም ከዚህ ውድድር ማግኘት ችሏል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የተካተቱት አረጋሽ ካሳና ፎዚያ መሐመድ ለዚህ ይጠቀሳሉ፡፡ ከሁለት ዓመታት በፊት በቢሾፍቱ በተከናወነው የመዝጊያ ጨዋታ ወቅት ከተመረጡት ወንድ ተጫዋቾች መካከል፣ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ  ማስፈረማቸው ታዳጊዎች ይታወሳሉ፡፡

ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በዝዋይ ከተማ በተጀመረውና በኮፓ ኮላ ማጠናቀቂያ ዙር፣ የመክፈቻ ጨዋታ ላይ በወንዶች የኦሮሚያ ክልል አማራ ክልልን 3ለ0 ሲረታ፣ በሴቶች ድሬዳዋና አፋር ሁለት አቻ ተለያይተዋል፡፡ 18  ቡድኖችን የሚያሳትፈው ሻምፒዮናው ቅዳሜ፣ ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ይጠናቀቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...