Monday, September 25, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትር

[የክቡር ሚኒስትሩ ሾፌር መኪና ውስጥ ዘፈን ከፍቷል]

  • ምን ዓይነት ሙዚቃ ነው አንተ?
  • ወደዱት ክቡር ሚኒስትር?
  • ያልተጠየከውን ምን ያስቀባጥርሃል? አማርኛ ዘፈን ነው ለመሆኑ?
  • አዎ ክቡር ሚኒስትር ራፕ ነው፡፡
  • ምንድነው ራፕ?
  • ዘመናዊ ሙዚቃ ነው፡፡
  • ይሰማሃል የሚለው ግን?
  • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፣ እርስዎ አይሰማዎትም?
  • ኧረ ምንም አይሰማኝም፡፡
  • ስለለመደብዎት ይሆናላ፡፡
  • ምኑ ነው የለመደብኝ?
  • አለማዳመጡ!

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው ገቡ] 

  • ፕሮፖዛሉ አልቋል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የትኛው ፕሮፖዛል?
  • የትልቁ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል፡፡
  • ስለዚህ ቀጣዩ ሥራ ምንድን ነው?
  • ያው ፕሮጀክቱን ማን ይገንባው የሚለው መወሰን አለበት፡፡
  • እሱማ ተወስኗል፡፡
  • ጨረታ እንዲወጣ ማለትዎ ነው?
  • የምን ጨረታ ነው የምትለው?
  • ማለቴ ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ሊገነባ የሚችል ተቋም ለማግኘት ነዋ፡፡
  • እኮ ምን ዓይነት ጨረታ?
  • ዓለም አቀፍ ጨረታ ነዋ፡፡
  • የኒዮሊብራሊስቶች ድርጅት መጥቶ ሊገነባ?
  • የአገር ውስጥ ጨረታም ማውጣት እንችላለን፡፡
  • እኮ የማንም ኪራይ ሰብሳቢ ድርጅት መጥቶ እንዲገነባው?
  • ታዲያ ማን ይገንባው ክቡር ሚኒስትር?
  • እኛው ያቋቋምነው ድርጅት ነዋ፡፡
  • ያለምንም ጨረታ?
  • ፕሮጀክቱ እኮ የመንግሥት ነው፡፡
  • ቢሆንስ ክቡር ሚኒስትር?
  • የመንግሥት ፕሮጀክት በመንግሥት ተቋም ነው መገንባት ያለበት፡፡
  • ከመቼ ጀምሮ?
  • አንተ ለመሆኑ ማን ነው ተቆጣጣሪ ያደረገህ?
  • እንዳያስጠይቀን ብዬ ነው፡፡
  • ስለእሱ አታስብ፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • ጠያቂውም መንግሥት ነው፤ መላሹም መንግሥት ነው፡፡
  • ሕዝቡስ?
  • ለሕዝቡማ ከባድ የቤት ሥራ ሰጥተነዋል፡፡
  • ምን ዓይነት የቤት ሥራ?
  • የኑሮ ውድነት የሚሉት፡፡
  • ግን ክቡር ሚኒስትር…
  • የምን ግን?
  • አሁን ይኼ ተቋም ይህን ትልቅ ፕሮጀክት ለመገንባት ከዚህ በፊት ምን ሠርቷል?
  • ምን ዓይነት ጥያቄ ነው?
  • ማለቴ ልምድ አለው ወይ?
  • እንዲህ ዓይነት ሥራ እየሠራ ልምድ ካልያዘ፣ እንዴት ልምድ ሊኖረው ይችላል?
  • ያው ይኼ ከባድ ሥራ ነው ብዬ ነው፡፡
  • ተቋሙ ከባድ የሚባል ነገር አያውቅም፤ ብረት ነው ስልህ፡፡
  • እንደ ተረቱ እንዳይሆን ብዬ ነው፡፡
  • ምንድን ነው ተረቱ?
  • መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ፡፡
  • እና እነሱ እንደስማቸው ብረት አይደሉም እያልከኝ ነው?
  • ሥጋት ስላለኝ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምኑ ነው የሚያሠጋህ?
  • አቅማቸው!

[ከክቡር ሚኒስትሩ ጋ የቦርድ አባል የሆኑ ሌላ ሚኒስትር ደወሉላቸው] 

  • ክቡር ሚኒስትር ምነው ከቦርድ ስብሰባው ቀሩ?
  • በጣም አፋጣኝ ሥራ ገጥሞኝ ነው፡፡
  • ያው አዲሱ ትልቅ ፕሮጀክት ወደ ሥራ እንዲገባ ተወስኗል፡፡
  • ማን ይሥራው ተባለ?
  • እሱ ገና አልተወሰነም፣ ግን በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
  • ምኑ ነው የሚያሳስበው?
  • ያው ፕሮጀክቱ ትልቅ ስለሆነ ማን ይገንባው የሚለው ነዋ፡፡
  • ምን ችግር አለው? የእኛው ድርጅት ይገነባዋላ፡፡
  • የትኛው ድርጅት?
  • ትልቁ ድርጅት ነዋ፡፡
  • እሱማ ሕፃን ነው እኮ፡፡
  • እኮ ሕፃን ልጅ እንዲያድግ ሥጋውንም፣ ወተቱንም፣ ፋፋውንም መመገብ አለብህ፡፡
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • ስለዚህ ይኼ ድርጅት እንዲያድግ ባቡሩንም፣ ግድቡንም፣ ፋብሪካውንም መመገብ አለብን፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በቃ አከበርኩዎት፡፡
  • ለዛ እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር የሚሉኝ፡፡
  • እኔማ ለእርስዎ አንድ ቃል ነው ያለኝ፡፡
  • ምን የሚል ቃል?
  • ብልህ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮጀክቶቹን የሚገነባው ድርጅት ኃላፊ ጋ ደወሉ] 

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • ጠፋህ እኮ ወዳጄ፡፡
  • ያው በርካታ ፕሮጀክቶች እኮ ተቀብለን ደፋ ቀና እያልን ነው፡፡
  • ሥራ በዛባችሁ አይደል?
  • ይኸው አገሪቷን እኮ በጫንቃችን ላይ ተሸክመናት ነው የምንዞረው፡፡
  • ይገባኛል እኛም ጫንቃችሁ እንዲጠነክር እኮ ነው በላይ በላይ የምናጐርሳችሁ፡፡
  • ሌላ የሚጐረስ ተገኘ እንዴ?
  • የሚጐረስማ በየጊዜው ነው ያለው፡፡
  • ዛሬ ምን ይዘው መጡ ታዲያ?
  • ትልቅ ፕሮጀክት እንዲሰጣችሁ አስደርጌያለሁ፡፡
  • ውለታዎትን በምን እንመልስ ታዲያ?
  • ያው ጀርባዬን ማከክማ እንዳትረሱ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር እዚህ የደረስነው እየታከክን አይደል እንዴ?
  • ለዛ ነው እኔም ጀርባዬን ማከክ አትርሱ ያልኩት፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር አሁንማ ጀርባዎትን በእጄ አይደለም የማክልዎት፡፡
  • ታዲያ በምን ልታከው ነው?
  • በኤክስካቫተር!
  • እንዲህ ከሆነማ ሌላም ፕሮጀክት በቅርቡ አጐርሳችኋለሁ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ጉርሻው ላይ ግን ጥንቃቄ መውሰድ አለብን፡፡
  • ምን ዓይነት ጥንቃቄ?
  • ብዙ አጉርሳችሁን በኋላ…
  • በኋላ ምን?
  • እንዳታስተፉን!

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ ቢሯቸው ገባች] 

  • ሰሙ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምኑን?
  • የክበባችን ወጥ ጨላፊ እኮ ሆስፒታል ገባች፡፡
  • ምን ሆና? አደጋ ደረሰባት እንዴ?
  • የለም የለም፣ እርጉዝ ስለሆነች ልትወልድ ነው፡፡
  • ውይ በጣም ደስ የሚል ዜና ነው የነገርሽኝ፡፡
  • ምን እናድርግላት ታዲያ?
  • በአስቸኳይ አማካሪዬን ጥሪልኝ፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ግብረ ኃይል መቋቋም አለበት፡፡
  • የምን ግብረ ኃይል?
  • ወጥ ጨላፊያችንን የሚያዋልድ ግብረ ኃይል!

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ተጠርቶ ቢሯቸው ገባ] 

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ስለፕሮጀክቱ እንድናወራ ብዬ ነው፡፡
  • ስለቅድሙ ፕሮጀክት ነው?
  • አይደለም፣ አዲስ ፕሮጀክት መጥቶልናል፡፡
  • የምን አዲስ ፕሮጀክት?
  • ወጥ ጨላፊያችን ልትወልድ ሆስፒታል ገብታለች፡፡
  • እሺ፡፡
  • ስለዚህ እሷን የሚያዋልድ ግብረ ኃይል መቋቋም አለበት፡፡
  • እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • የምን ቀልድ ነው? ስማ የእሷን ጉዳይ የሚከታተል ኮሚቴ መቋቋም አለበት፡፡
  • አወላለዷን የሚከታተል ኮሚቴ እያሉኝ ነው?
  • እህሳ፣ አንደኛው የመልካም አስተዳደር ችግር እኮ ይህ ነው፡፡
  • ምን እያሉ ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • ይኸው ኮሚቴ እንዴት ይቋቋማል እያልከኝ ነዋ?
  • ገርሞኝ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ስማ አንድም እናት በወሊድ መሞት የለባትም እያልን አሁን ለምን ኮሚቴ ይቋቋማል ትላለህ?
  • እሺ ምን ዓይነት ኮሚቴ ነው የሚቋቋመው?
  • ሦስት ኮሚቴ መቋቋም አለበት፡፡
  • ይንገሩኝ እስቲ፡፡
  • አንደኛ የገንፎ አስገንፊ ኮሚቴ፡፡
  • እ…
  • ሁለተኛ የአጥሚት ዝግጅት ኮሚቴ፡፡
  • እ…
  • ሦስተኛ የዳይፐርና ዋይፐር አፈላላጊና ገዢ ኮሚቴ፡፡

[የገንፎ አስገንፊ ኮሚቴው ኃላፊ ክቡር ሚኒስትር ቢሮ ገባ] 

  • ለመሆኑ ይኼን ኮሚቴ ለመምራት ምን ብቃት አለህ?
  • ክቡር ሚኒስትር ቁርስ፣ ምሳ፣ እራቴን ከገንፎ ውጪ አልበላም፡፡
  • ለነገሩ ፊትህ ራሱ እንደገንፎ የተነፋ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የተሰጠኝን ኃላፊነት ለመወጣት ከተማ ውስጥ አሉ የተባሉ የገንፎ እህሎችን ከነዋጋቸው አጣርቻለሁ፡፡
  • በጣም ደስ ይላል፡፡
  • እና በኤክስፖርት ስታንዳርድ ያለ የገንፎ እህል አግኝቻለሁ፡፡
  • ስማ ሥራህን እንዲህ በትጋት የምትሠራ ከሆነ ይኼን ኮሚቴ አሳድገዋለሁ፡፡
  • ወደ ምንድን ነው የምታሳድጉት ክቡር ሚኒስትር?
  • ወደ ገንፎ አስገንፊ ኮርፖሬሽን!

[የአጥሚት ዝግጅት ኮሚቴ ኃላፊዋ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባች] 

  • በአማካሪዬ በጣም ተደስቻለሁ፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • የፆታን ተዋፅኦ ከግምት ውስጥ ያስገባ ኮሚቴ ነው ያቋቋመው፡፡
  • ያው ክቡር ሚኒስትር እኔ በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ነው ያለኝ፡፡
  • ትንሽ ብታብራሪልኝ?
  • በአፌ ጁስ የሚባል ቀምሼ አላውቅም፡፡
  • ምንድን ነው የምትጠጪው ታዲያ?
  • አጥሚት ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እና ምን ይዘሽ መጥተሻል?
  • ያው ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሁሉ የሚበቃ የአጥሚት እህል ተዘጋጅቷል፡፡
  • በዚህ ትጋትሽ ከቀጠልሽ ኮሚቴውን አሳድገዋለሁ፡፡
  • ወደ ምንድን ነው የሚያሳድጉት?
  • ወደ አጥሚት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት!

[የዳይፐርና ዋይፐር አፈላላጊና ገዢ ኮሚቴ ኃላፊው ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ገባ] 

  • ይህን ኮሚቴ ለመምራት ምን ብቃት አለህ?
  • ክቡር ሚኒስትር አያስታውሱም እንዴ ግምገማ ላይ ምን ያህል ጊዜ ሽንት ቤት እንደምመላለስ?
  • ሽንታም ነኝ እያልከኝ ነው?
  • ከሙስናዬ ብዛት በግምገማ ወቅት በሽንት ብቻ መገላገሌ ዕድለኛ ነኝ፡፡
  • ስለዚህ ምን አስበሃል?
  • ዳይፐርና ዋይፐር ከውጭ ለማምጣት የውጭ ምንዛሪ ስለሚጠይቀን ሌላ ሐሳብ አለኝ፡፡
  • ምንድን ነው ሐሳብህ?
  • ያ ትልቁ ድርጅት ለምን ዳይፐርና ዋይፐር እዚሁ አገር ውስጥ አያመርትም?
  • የሚገርም ሐሳብ ነው ያመጣኸው እባክህ?
  • እዚህ ብናመርተው የውጭ ምንዛሪ ማትረፍ እንችላለን ብዬ ነው፡፡
  • አሁኑኑ ወደ ምርት መገባት አለበት፡፡
  • ሐሳቤን ስለተቀበሉኝ አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ከዛሬ ጀምሮ አንተም የእኔ ልዩ አማካሪ ሆነሃል፡፡
  • በምን ጉዳይ ክቡር ሚኒስትር?
  • በዳይፐርና ዋይፐር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በቀይ ባህር ፖለቲካ ላይ በመከረው የመጀመሪያ ጉባዔ ለዲፕሎማቲክና ለትብብር አማራጮች ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ ቀረበ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ለመጀመርያ ጊዜ በቀይ ባህር ቀጣና የፀጥታ...

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...

የመጀመርያ ምዕራፉ የተጠናቀቀው አዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ተከላው እንደገና ሊከናወን መሆኑ ተሰማ

እስካሁን የሳር ተከላውን ጨምሮ 43 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል ዕድሳቱ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን የፓርቲያቸውን የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ አጠናቀው ወደ ቢሯቸው ሲመለሱ ቢሯቸው ውስጥ አማካሪያቸው አንድ ጽሑፍ በተመስጦ እያነበበ አገኙት]

ምንድነው እንደዚህ መስጦ የያዘህ ጉዳይ? መጡ እንዴ ክቡር ሚኒስትር፣ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ እያነበብኩ ነው፡፡ ግን እኮ ፊትህ ላይ የመገረም ስሜት ይነበባል፡፡ አዎ፣ መግለጫው ላይ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን ሞባይል ስልካቸውን ተመለከቱ፣ የህዳሴ ግድቡ ተደራዳሪ መሆናቸውን ሲያውቁ ስልኩን አነሱት]

ሃሎ... ጤና ይስልጥኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስልጥልኝ ክቡር ተደራዳሪ... የጥረትዎን ፍሬ በማየትዎ እንኳን ደስ አለዎት፡፡ እንኳን አብሮ ደስ አለን፣ ምን ልታዘዝ ታዲያ? የውኃ ሙሌቱንና አጠቃላይ የግድቡን የግንባታ ሁኔታ...

[የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ ክቡር ሚኒስትር ሌሊቱን በእንቅልፍ ልባቸው በህልም እየተወራጩ ሳለ የሞባይል ስልካቸው ጥሪ አነቃቸው። አለቃቸው ስለነበሩ ስልኩን በፍጥነት አነሱት]

በሌሊት ስለደወልኩኝ ይቅርታ፡፡ ችግር የለውም ክቡር ሚኒስትር፣ ምን ልታዘዝ? አንድ የአውሮፓ ባለሥልጣን ነገ በጠዋት ወደ አዲስ አበባ ይገባል። እሺ። ሌሎች የመንግሥት አመራሮች ስላልቻሉ እርስዎ መንግሥትን ወክለው ቦሌ ኤርፖርት...