የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎች
ሩብ ኪሎ በአራት መዓዘን ተከትፎ የተጠበሰ ቀይ ስር
ሩብ ኪሎ በቁመቱ ተከትፎ የተጠበሰ ቀይ ሽንኩርት
አንድ ታጥቦ የተዘጋጀ ሰላጣ
ሦስት ተልጦ በዓራት መዓዘን የተከተፈ ቲማቲም
አንድ የሻይ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ሲኒ ዘይት
አንድ የሻይ ማንኪያ ጨውና ቁንዶ በርበሬ የተደባለቀ
አራት ተቆራርጦ የተጠበሰ ዳቦ
አዘገጃጀት
በጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ የተዘጋጀውን ቀይ ስር፣ ቲማቲም፣ ሰላጣና ቀይ ሽንኩርት ማደባለቅ፡፡ በሌላ ሳህን ላይ ሆምጣጤ፣ ጨው፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቁንዶ በርበሬ እና ዘይት እስኪወፍር ድረስ መምታት፡፡ ከሰላጣው ጋር በማዋሃደ ከተጠበሰው ዳቦ ጋር መመገብ፡፡