Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊዘጠኝ የአፍሪካ አገሮች ለፕሮጀክቶቻቸው ማስፈጸሚያ የስድስት ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አገኙ

ዘጠኝ የአፍሪካ አገሮች ለፕሮጀክቶቻቸው ማስፈጸሚያ የስድስት ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አገኙ

ቀን:

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ዘጠኝ የአፍሪካ አገሮች በምግብ ዋስትና፣ በተመጣጠነ ምግብና በኢነርጂ ዙሪያ ለመሥራት የወጠኗቸውን መነሻዎች፣ ከዓለም አቀፉ የዘላቂ ልማት (ሰስተነብል ዴቨሎፕመንት) ግቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለማከናወን የሚያስችሏቸውን የአራት ዓመት የሙከራ ፕሮጀክቶቻቸውን ቀረፁ፡፡ ፕሮጀክቶቹን ተግባራዊ ለማድረግ የፈረንሣይ መንግሥት የስድስት ሚሊዮን ዩሮ ድጋድ አድርጓል፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እስከ 2012 ዓ.ም. ድረስ በሥራ ላይ የሚቆዩትን እነዚህን ፕሮጀክቶች የቀረፁት ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሌሴቶ፣ ማላዊ፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳንና ኡጋንዳ ናቸው፡፡ ቀረፃውም የተካሄው አዲስ አበባ ውስጥ ከግንቦት 10 ቀን እስከ ግንቦት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በተካሄደው አህጉራዊ ዐውደ ጥናት ላይ ነው፡፡

የየአገሮቹ ተወካዮች ተሳታፊ በሆኑበትና በዓለም አቀፍ የከብት ሀብት ልማት ማዕከል የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው በዚሁ ዐውደ ጥናት ላይ ፕሮጀክቶቹ የተቀረፁት፣ የየአገሮቹ መነሻ ሐሳቦች ቀርበው በታዳሚዎች ሰፋ ያለ ግምገማ፣ ውይይትና የሐሳብ መለዋወጥ ከተደረገባቸው በኋላ ነው፡፡

- Advertisement -

ከቀረቡትም የመነሻ ሐሳቦች መካከል ‹‹ኢንትግሬትድ ወተር ሪሶርስ ማኔጅመንት ፎር ትራንስባውንደሪ ወተር ኮኦፕሬሽን ኢን ገናሌ ዳዋ ሪቨር ቤዚን›› በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ ያቀረበችው የመነሻ ሐሳብ ይገኝበታል፡፡ ይህንን የመነሻ ሐሳብ የቀረፀው የኢትዮጵያ ካንትሪ ወተር ፓርትነርሺፕ ከወተር ኤንድ ላንድ ሪሶርስ ሴንተር ጋር በመተባበር ነው፡፡

ዶክተር ጠና አላምረው የኢትዮጵያ ካንትሪ ወተር ፓርትነርሺፕ ዋና ጸሐፊና የወተር ኤንድ ላንድ ሪሶርስ ሴንተር ምክትል ዳይሬክተር በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘጠኙ አገሮች ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ የተቀረፁት እነዚሁ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ የሚሆኑት፣ ከፈረንሣይ መንግሥት በተገኘ የስድስት ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ነው፡፡

የፕሮጀክቶቹ የሙከራ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ እንደገና ለማራዘም የሚያስችል ድጋፍ የማፈላለጉ ሥራ ይካሄዳል፡፡  ይህንንም ሥራ የሚያካሂዱት በተባበሩት መንግሥታት የእርሻና የምግብ ድርጅት (ፋኦ)፣ የአፍሪካ ኅብረትና ኢንተርናሽናል ወተር ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ናቸው፡፡

ዘጠኙ አገሮች የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ፕሮጀክቶች እንዲቀርፁ የተደረገበት ምክንያት፣ በዘርፉ የተሻለ ሥራ ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት ነው፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭነታቸውና የዘላቂ ልማት ግቦችን ከዳር ለማድረስ ቁርጠኛ ሆነው መገኘታቸው ለፕሮጀክቶቻቸው ቀረፃ ሌላው መንስዔ መሆኑን ዶ/ር ጠና ተናግረዋል፡፡

የውኃ፣ የመስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጀምስ ደንግቾል ቶት  ዐውደ ጥናቱን ሲከፍቱ፣ ‹‹ኤሊኖ ከድርቅ ጋር ተያይዞ ያስከተለው ተፅዕኖ በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ አምስት አገሮች ውስጥ የሚኖሩትንና ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሕዝቦችን ለምግብ እጥረት ተጋላጭ አድርጓቸዋል፤›› ብለዋል፡፡

ለዚህ ዓይነቱ ችግርና አደጋ ተጋላጭ የሆኑትም በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በጂቡቲ፣ በሰሜን ሶማሊያና በከፊል ሱዳን የሚገኙ ሕዝቦች መሆናቸውንና ከኤሊኖ አስቀድሞ ወይም በቅድመ ኤሊኖ በደቡብ አፍሪካ ማላዊ፣ ዚምባቡዌ፣ ሞዛምቢክ፣ ማዳጋስካርና ሌሴቶ የሚገኙ 28 ሚሊዮን ሕዝቦች ለምግብ እጥረት እንደተጋለጡ አስረድተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል 2.5 ሚሊዮን ያህሉ አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሆነው መገኘታቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመው፣ በዚህ ችግር ላይ የኤሊኖ ተፅዕኖ ሲታከልበት የጉዳቱን መጠን ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

አፍሪካ ውስጥ ከ600 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ካለው የእርሻ መሬት መካከል 80 በመቶ ያህሉ የሚለማው አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች አማካይነት እንደሆነና ከዚህ አኳያ ግብርና ለድህነት ቅነሳ የሚኖረውን ፋይዳ አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

ኤሊኖ በዓለም የአየር ንብረት ላይ ድንገተኛ የሆነ አደጋ የማሳደሩን፣ ተፅዕኖው እንደሚቀጥልና ይህ ዓይነቱም ተፅዕኖ በጤና፣ በውኃ አቅርቦትና በምግብ ዋስትና ላይ ችግር የሚያስከትል መሆን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉት አገሮች ውስጥ ጠንካራና ቀጣይነት ላለው የምግብ ዋስትና መረጋገጥ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬታማነት የተቀናጀ ሥራ ማከናወን አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...