Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየማራቶን ብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

የማራቶን ብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ

ቀን:

ከ200 በላይ የዓለም አገሮች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቀው 31ኛው ኦሊምፒያድ በመጪው ክረምት በብራዚል ሪዮ ከተማ አስተናጋጅነት በይፋ ይጀመራል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጊዜያዊ የብሔራዊ አትሌቶችን ዝርዝር ይፋ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የማራቶን ተወዳዳሪዎች ማንነት አሳውቋል፡፡

ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንደተገኘው መረጃ ከሆነ በሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ውጤት ታስመዘግብበታለች ተብሎ በሚጠበቀው ማራቶን የተወዳዳሪዎች ጊዜያዊ ዝርዝር ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች የመጀመርያው ተመራጭ የ24 ዓመቱ ተስፋዬ አበራ ሆኗል፡፡ አትሌቱ በያዝነው የውድድር ዓመት በዱባይና ሐምቡርግ ማራቶኖች ተወዳድሮ 2፡04፡24 እና 2፡06፡58 ወቅታዊ ሰዓቱ ነው፡፡ በተራ ቁጥር ሁለት የተቀመጠውና የ21 ዓመቱ ለሚ ብርሃኑ በውድድር ዓመቱ በዱባይና ቦስተን ማራቶኖች ተወዳድሮ 2፡04፡33 እና 2፡12፡45 ወቅታዊ ሰዓት ተወስዶለታል፡፡ የ26 ዓመቱ ደሲሳ ፈይሳ ደግሞ በውድድር ዓመቱ በቶኪዮ ማራቶን ተወዳድሮ 2፣06፣56 ወቅታዊ ሰዓቱ ሲሆን፣ በዱባይ ማራቶን 2፡06፡35፣ በሮተርዳም ማራቶን 2፡09፡55 እና በርሊን ማራቶን 2፡06፡57 ያስመዘገበው የቅርብ ጊዜ ሰዓቶቹ ናቸው፡፡ በተራ ቁጥር አራት የተቀመጠው የ33 ዓመቱ ቀነኒሳ በቀለ በውድድር ዓመቱ በለንደን ማራቶን ተወዳድሮ 2፣06፡36 ያስመዘገበው ወቅታዊ ሰዓት ተይዞለታል፡፡ የ31 ዓመቱ የማነ ፀጋዬ በውድድር ዓመቱ በተከናወነው ቦስተን ማራቶን 2፡14፡02 ወቅታዊ ሰዓቱ ሆኗል፡፡ ስድስተኛ ሆኖ የተመረጠው ሌሊሳ ዲሳሳ በውድድር ዓመቱ በተከናወነው ቦስተን ማራቶን 2፣13፣32 ወቅታዊ ሰዓቱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በሴቶች በፌዴሬሽኑ የመጀመርያ ተመራጭ የሆነችውና የ26 ዓመቷ ማሬ ዲባባ በውድድር ዓመቱ በተከናወነው ለንደን ማራቶን 2፡24፡09 እና የዓምናው የቦስተን ማራቶን 2፡24፡59 ወቅታዊ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በተራ ቁጥር ሁለት የተቀመጠችውና የ31 ዓመቷ አሰለፈች መርጊያ በውድድር ዓመቱ በተከናወነው ለንደን ማራቶን 2፡23፡57 እና ዓምና በዱባይ ማራቶን ያስመዘገበችው 2፡20፡02 ወቅታዊ ሰዓቷ ነው፡፡ ቀጣዩን ተራ ቁጥር የያዘችው የ29 ዓመቷ አበሩ ከበደ ነች፡፡ አትሌቷ በውድድር ዓመቱ በተከናወነው ቶኪዮ ማራቶን 2፡23፡01 እና ዓምና ዱባይ ማራቶን 2፡21፡17 ያስመዘገበችው ሰዓት ተቀምጧል፡፡ የ31 ዓመቷ ትርፊ ፀጋዬ በውድድር ዓመቱ በተካፈለችበት ዱባይ ማራቶን 2፡19፡41 እንዲሁም ዓምና በቦስተን ማራቶን 2፡30፡03 ወቅታዊ ሰዓቷ ሆኗል፡፡ በመጨረሻም የ29 ዓመቷ ትዕግሥት ቱፋ በውድድር ዓመቱ በተካፈለችበት ለንደን ማራቶን 2፡23፡03 ወቅታዊ ሰዓት ተይዞላታል፡፡ በመጨረሻም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አያይዞ እንደገለጸው ከሆነ፣ ምርጫውን ተከትሎ ቅሬታ ያላቸው አትሌቶች እስከ ሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ በአካል ቀርበው፣ የሚመለከተውን አካል ማነጋገር ይችላሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...

ማን ይቻለን?

በጠዋት የተሳፈርንበት ታክሲ ውስጥ በተከፈተው ሬዲዮ፣ ‹‹ይኼኛው ተራራ ያን...