Saturday, September 30, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቱርክ በረራ ሊጀምር ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቱርክ ዋና ከተማ ኢስታንቡል በሳምንት ሦስት ቀናት በረራ ሊጀምር እንደሆነ ገለጸ፡፡

አየር መንገዱ የቱርክ የታሪክ፣ የኢንዱስትሪና የፋይናንስ ከተማ ወደ ሆነችው ኢስታንቡል የሚበረው በቦይንግ 737-800 አውሮፕላን መሆኑም ታውቋል፡፡

ወደ ኢስታንቡል አዲስ በረራ በመጀመሩ መደሰታቸውን የገለጹት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ አዲሱ በረራ የቱርክ አየር መንገድ በየቀኑ እየሰጠ የሚገኘውን የበረራ አገልግሎት የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡ ቱርክ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ አገሮች ተርታ የምትሰለፍ በመሆኗ፣ አዲሱ በረራ የሁለቱን አገሮች ኢንቨስተሮች በማገናኘት የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ92 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲኖሩት፣ አምስት አኅጉራትን በበረራ ያገናኛል፡፡ አየር መንገዱ የበረራ መዳረሻዎቹን እያስፋፋ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ወደ ቶኪዮ፣ ማኒላ፣ ዳብሊን፣ ኬፕ ታውንና ሎስ አንጀለስ የበረራ አገልግሎት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በቅርቡም አየር መንገዱ ወደ ኒውዮርክ ከተማ በሳምንት ሦስቴ ለመብረር አቅዷል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች