‹‹ለመመረጡ፣ ለስኬቱ እንዲሁም ይህን ከፍተኛ ኃላፊነት ከነከባድ ተግዳሮቱ ለመቀበል በመብቃቱ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ለሚስተር ማክሮን ደውዬለት ነበር፡፡››
በዘንድሮው የፈረንሣይ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸናፊዋ ማሪን ለፔን፣ ከሽንፈታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት፡፡ ሚያዝያ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኢማኑኤል ማክሮን አዲሱ የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ለመሆን የበቁት የቅርብ ተቀናቃኛቸውንና የቀኝ አክራሪ ፓርቲ ብሔርተኛዋን ማሪ ለፔንን ከ66 በመቶ በላይ የምርጫ ድምፅ አግኝተው በማሸነፍ ነው፡፡ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ቃለ መሐላቸውን ቅዳሜ ግንቦት 6 ቀን ይፈጽማሉ፡፡