አርሶ አደሩ አቶ ዳዲ ጅራ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከአዳማ ከተማ አቅራቢያ (ወንጂ ማዞርያ) በ65 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነቡት ሆቴል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ደምበል ቪው ኢንተርናሽናል በሚል የተሰየመው ሆቴል፣ ጥንድ ሕንፃና ባለ ሰባት ፎቅ ነው፡፡ 55 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች፣ አራት የመሰብሰቢያ አዳራሾችን ይዟል፡፡ በመቂ ከተማ የቲማቲምና የፍራፍሬ ማሳ ባለቤት የሆኑት አርሶ አደሩ አቶ ዳዲ፣ ለሆቴሉ የምግብ ዝግጅት ከማሳቸው እንደሚጠቀሙ፣ በምርቃቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡ ከአዳማ ከተማ አንድ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው አዲሱ ሆቴል ሚያዝያ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባ ዱላ ገመዳና የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቆ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
ፎቶ፡- በዳንኤል ጌታቸው