Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኦነግና ኦፌኮ አብሮ ለመሥራት ንግግር ጀመሩ

ኦነግና ኦፌኮ አብሮ ለመሥራት ንግግር ጀመሩ

ቀን:

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የመጀመርያ ምክክር ማድረግ መጀመሩን፣ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላት ገመቹ ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡

ከኦነግ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥሪ ተቀብለው ወደ አገር ውስጥ እየገቡ ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እየተነጋገሩ እንደሆነ አቶ ሙላት ገልጸዋል፡፡

‹‹ከኦነግ ጋር በተመለከተ የተቀራረበ የፖለቲካ ፕሮግራም ስላለን፣ እንዲሁም የኦሮሞን ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አንድ ላይ ተቀራርበን ብንሠራ የተሻለ እንደሚሆን በሕዝቡ ስለሚነግረን የተጀመረ ንግግር ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሆኖም ሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሚያስቀምጣቸው ሦስት መሥፈርቶች ማለትም ፍፁም ውህደት፣ ቅንጅት ወይም ግንባር በሚለው ጉዳይ ላይ በንግግር ደረጃ የሚገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ምን እንደሚሆን ወደፊት የሚወሰን ይሆናል ሲሉ ምክትል ሊቀመንበሩ አስረድተዋል፡፡

የመጀመርያው የሁለቱ ድርጅቶች ውይይት በፍፁም መስማማት የተከናወነ እንደሆነና በርካታ ተስፋ ሰጪ ግብዓቶች የተገኙበት ነበር ብለዋል፡፡

‹‹ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ፓርቲዎችም ሆነ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነን፤›› ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ አገር ቤት ከገቡ ፓርቲዎች መካከል ለኦሮሞ ሕዝብ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር በቀጣይ አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች መነጋገር መጀመራቸውንም አክለዋል፡፡

ፓርቲዎች ተደራጅተው በአንድነት መምጣታቸው ለሚያስመዘግቡት ውጤት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረውና መራጩ ሕዝብም የሚጠቀ

ምበት ይሆናል በማለት፣ ፓርቲዎቹ አብሮ ለመሥራት የሚያደርጉት ጥረት ጠንካራ የፖለቲካ ኃይል ለመሆን የሚደረግ እንቅስቃሴ እንደሆነም አውስተዋል፡፡

መንግሥት በኤርትራ ከነበሩት የኦነግ አመራሮች ጋር በቅርቡ የሰላም ስምምነት መፈራረሙ የሚታወስ ሲሆን፣ መቀመጫቸውን ኤርትራ ያደረጉ የኦነግ አመራሮች በቅርቡ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱና የአቀባበል ኮሚቴ መቋቋሙ ታውቋል፡፡

ኦነግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ተፈርጆ የነበረ፣ በቅርቡ ደግሞ አሸባሪ የሚለው ስያሜ የተነሳለት አንጋፋ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ