Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ወደ ፌዴራል መንግሥት ተዘዋውረው የነበሩ መሥሪያ ቤቶቹን መሰብሰብ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ወደ ፌዴራል መንግሥት ተዘዋውረው የነበሩ መሥሪያ ቤቶቹን መሰብሰብ ጀመረ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አንበሳ አውቶብሳ ድርጅት በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲመለስ በ2003 ዓ.ም. ቢወስንም ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ፣ የምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ካቢኔ ድርጅቱ ደንብና መመርያ ወጥቶለት በቀጥታ ተጠሪነቱ ለከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን ወሰነ፡፡

ከአወዛጋቢው ምርጫ 97 በኋላ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ፌዴራል መንግሥት እንዲዛወሩ የተደረጉ ተቋማት ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ እንዲሁም አንበሳ የከተማ አውቶብስ ድርጅትና ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ የተለያዩ አሠራሮች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ሥልጣን ከተረከቡ በኋላ በወሰዷቸው የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ፌዴራል ሄደው የነበሩ መሥሪያ ቤቶችንና አሠራሮችን ለመመለስ በወሰዱት ዕርምጃ፣ በተለያዩ ችግሮች ተተብትቦ የሚገኘው አንበሳ አውቶብስ ድርጅት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት ቀደም ሲል በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር ይተዳደር ነበር፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሥሩ ሲተዳደር የቆየው የጅማ ከተማ አንበሳ አውቶብስ ድርጅትም ራሱን ችሎ እንዲደራጅ ተወስኖ ነበር፡፡

ነገር ግን ውሳኔው በተለያዩ መሰናክሎች ተግባዊ ሳይደረግ ቆይቶ፣ በሥራ አመራር ቦርድና በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ሲመራ ቆይቷል፡፡

አዲሱ ካቢኔ ግን የአንበሳ አውቶብስ ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንዲመለስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ካቢኔው አካሂዶ በነበረው ውይይት የድርጅቱ ተጠሪነት በቀጥታ ለትራንስፖርትና መንገዶች ቢሮ እንዲሆን ሐሳብ ቢቀርብም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አንበሳ አውቶብስ ድርጅት ተጠሪነቱ ለከተማው ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን በመደንገጉ ሐሳቡ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

ለትራንስፖርትና መንገዶች ባለሥልጣን ተጠሪ መሆን ካለበት በቅድሚያ ቻርተሩ መሻሻል ይኖርበታል ሲሉ፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አሁንም ያለየለት ጉዳይ ግን የጅማ ከተማ አውቶብሰስ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ነው፡፡ ከ40 ዓመታት በላይ ለጅማ ከተማና ለአጎራባች ወረዳዎች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የጅማ ቅርንጫፍ፣ በቀጥታ ድጎማ ሲደረግለት የቆየው በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ ድርጅት ነው፡፡

ነገር ግን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሁለቱ ተቋማት እንዲለያዩ በመወሰኑ፣ የጅማ ቅርንጫፍ በድጎማ ዕጦት ከመስመር እየወጣ ነው፡፡

የችግሩ ዋና ማሳያ በተለይ ከጅማ ከተማ ሰርቦ፣ ሰቃ፣ ዴዶና የቡ ከተሞች ድረስ የሚደረጉ የአውቶብስ ጉዞዎች የተቆራረጡ በመሆናቸው ቅሬታ እየቀረበ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የ2010 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት የኦዲት ግኝት ሪፖርት፣ አንበሳ አውቶብስ ድርጅት ከባድ ችግር ውስጥ ነው፡፡

ለአብነት ከተጠቀሱት ውስጥ በ2009 ዓ.ም. በመካኒሳ ዴፖ በሚገኘው የጥገና ጋራዥ ላይ በደረሰው ቃጠሎ ለወደሙ አውቶበሶች የመድን ዋስትና ባለመገባቱ 8.7 ሚሊዮን ብር ከስሯል፡፡

 በታኅሳስ 2005 ዓ.ም. ከግብፅ የተገዙ የዳፍ አውቶብስ ሞተሮች ለ50 አውቶብሶች የተገጠሙ ቢሆንም፣ ከእነዚህ ውስጥ ለ21 ዳፍ አወቶብሶች 14.2 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ የተገጠሙ ሞተሮች ስድስት ወራት ሳያገለግሉ ተበላሽተዋል፡፡

ከ29.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የአውቶብስ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ከ15 ዓመት በላይ አገልግሎት ላይ ሳይውሉ ወይም ሳይወገዱ ተገኝተዋል የሚሉት ተጠቃሾች የኦዲት ግኝቶች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...