Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታ ሰጠ

የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁንታ ሰጠ

ቀን:

በቻይና አፍሪካ የልማት ፎረም ላይ ለመሳተፍ በአገሪቱ ዋና ከተማ ቤጂንግ ለቀናት ቆይታ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያን የሚጠቅሙ በርከት ያሉ ስምምነቶችን ማድረግ መቻላቸው ታወቀ፡፡ የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ይሁንታ እንደሰጣቸው ተሰምቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእሑድ ነሐሴ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና በነበራቸው ቆይታ ከተገኙት ስኬቶች መካከል፣ ኢትዮጵያ ያለባትን የቻይና ዕዳ በተመለከተ ላቀረቡት ጥያቄ ቻይና የይሁንታ ምላሽ መስጠቷ አንዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እሑድ ዕለት ከቻይና ኤግዚም ባንክ ሊቀመንበር ሁ ዢአኦዚን ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ባንኩ ለኢትዮጵያ የሰጣቸውን ብድሮች የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምና የወለድ ምጣኔውም እንዲቀንስላቸው ጥያቄ አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያ ከቻይና ያገኘቻቸውን ብድሮች የሚገዙ ስምምነቶች በሁለቱ አገሮች ስምምነት መሻሻል የሚችሉ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከፍተኛ የውጭ ብድር ጫና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የደቀነውን ሥጋት በዋናነት በማንሳት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄያቸውን እንዳቀረቡ ምንጮች አስረድተዋል፡፡

የባንኩ ሊቀመንበር የቀረበውን ጥያቄ ሙሉ  በሙሉ እንደሚቀበሉትና ዝርዝር አፈጻጸሙን በተመለከተ፣ ሁለቱም አገሮች በሚመድቧቸው ልዑካን ወይም ኮሚቴ በዝርዝር እንዲታይ ይሁንታ መስጠታቸው ተገልጿል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ይኼንኑ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ከቻይና አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኬክያንግ ጋር የተናጠል ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅትም ቻይና የኢትዮጵያ ልዩ አገር ሆና እንደምትቀጥልና በቀጣዮቹ ዓመታት ቻይና በኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ማስፋፋት፣ በግብርና፣ እንዲሁም በነዳጅ ፍለጋ መስኮች ትኩረት አድርጋ እንደምትንቀሳቀስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማረጋገጣቸው ታውቋል፡፡ የቻይና አፍሪካ የልማት ፎረም መድረክ ላይ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ይፋ ያደረጓቸው የልማት ፕሮግራሞችና የዕዳ ስረዛው ኢትዮጵያን ሊጠቅም እንደሚችል የዲፕሎማቲክ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር በመድረኩ ይፋ ካደረጉት አንዱ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ እንዲሁም ወደብ አልባና ከቻይና ጋር ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ያላቸው የአፍሪካ አገሮች ከቻይና የወሰዱት ብድር የሚሰረዝ መሆኑ ነው፡፡

የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር በይፋ እንደተናገሩት እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ መከፈል የሚጀምር ዕዳ ያለባቸው እነዚህ አገሮች ዕዳቸው ቀሪ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ ከቻይና የወሰደችው ብድር ካለባት 25 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ከመያዝ ባለፈ፣ ዋናውን ብድርና ወለድ የመክፈል ግዴታ ውስጥ መግባቷንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ለአብነት ያህል በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. እንደ ቅደም ተከተላቸው 1.1 ቢሊዮን እና 1.2 ቢሊዮን ዶላር የዋና ብድርና የወለድ ክፍያ መፈጸሟን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ከቻይና የተገኘው ይሁንታ የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና በማቅለል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ሲኖረው፣ ይህም የተጓተቱ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ የፋይናንስ ፍላጎትን ያስገኛል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በቻይና ቆይታቸው ከሱዳንና ግብፅ መሪዎች ጋር በተናጠል ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...