Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበአካል ጉዳተኞች ስም ሙስና እየተፈጸመ መሆኑ ተነገረ

በአካል ጉዳተኞች ስም ሙስና እየተፈጸመ መሆኑ ተነገረ

ቀን:

በኢትዮጵያ በሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ስም ከተለያዩ የዓለም አገሮች በርከት ያለ የገንዘብና የቁሳቁስ ዕርዳታ የሚገኝ ቢሆንም፣ እነሱን መነሻ አድርገው ለተቋቋሙ ድርጅቶች መጠቀሚያ የሚውል መሆኑንና ይህም ድርጊት ሙስና እንደሆነ አካል ጉዳተኞች ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአካል ጉዳት መሆናቸው በተለዩት የጉዳት ዓይነቶች በርካታ ዕርዳታዎች የሚለገሱ ቢሆንም፣ ተጎጂዎቹ የተጠቀሙና ለውጥ ያመጡበት የሚያስመስሉ ሐሰተኛ ሪፖርቶች ከመሰማታቸው ባለፈ፣ የግለሰቦች ጥቅም ማስጠበቂያና የግል ሀብት ማከማቻ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ ‹አካል ጉዳተኞች በፀረ ሙስና ትግሉ እኩል ተሳታፊነታቸውን ለማረጋገጥ› በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐርመኒ ሆቴል ባዘጋጀው የአንድ ቀን የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች፣ ባለድርሻ አካላትና የተለያዩ ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

- Advertisement -

‹‹አካል ጉዳተኝነት፣ ሙስናና የአካታች ልማት ጽንሰ ሐሳብ›› የሚል ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል መምህር ዓለማየሁ ተክለ ማርያም (ዶ/ር)፣ በአካል ጉዳተኞች ስም ከውጭ የሚመጣ ገንዘብና ቁሳቁስ ለንግድ ይውላል ብለዋል፡፡ ይኼ ደግሞ ዓይን ያወጣ ሙስና መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አካል ጉዳተኞችን በስማቸው የተገኘን ነገር እንዳይጠቀሙ ማድረግ፣ መንግሥት ያወጣውን ፖሊሲ አለማስፈጸም፣ አድልኦ መፍጠር፣ ታማኝ አለመሆንና ጥገኛ እንዲሆኑ ማድረግም ሙስና መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በአካል ጉዳተኞች ላይ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመ እንደሚገኝ የጠቆሙት የዓውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች፣ ከትምህርት አሰጣጥ ጀምሮ አጠቃላይ አኗኗራቸውን በሚመለከት መንግሥት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ በእነሱ ስም ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን ማንኛውንም ዓይነት ዕርዳታ በአግባቡ ተቀብሎና ተቆጣጥሮ፣ ለእነሱ ተደራሽ የሚሆንበት አሠራር ሊዘረጋ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ትምህርትን በሚመለከት የሚመለከተው አስፈጻሚ ትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም ሳይደብቅ ‹‹በአካል ጉዳተኛ ላይ አልተሠራም ወይም አልሠራሁም›› ብሎ ማመኑ ጥሩ መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹አልሠራሁም›› እያሉ ዓመታዊ ሪፖርት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ስህተቱን አርሞ ከልብ መሥራት መጀመር ግድ እንደሚል አሳስበዋል፡፡

ለአካል ጉዳተኞች እየሠሩ መሆናቸውን በስማቸው የተቋቋሙ ፌዴሬሽኖችና ማኅበራት እየተናገሩ ቢሆንም ሥራው በትምህርት፣ በሥልጠናና በተለያዩ ነገሮች የታገዘ ሳይሆን የጉልበት ብዝበዛ መሆኑን ጠቁመው፣ ይኼም ሙስና መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መንግሥት ግን ክትትል አድርጎ ተገቢውን ማስተካከያ ሊያደርግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት ቢጋብዙም የመሳተፍ ፍላጎታቸው እስከዚህም መሆኑን የጠቆሙ የትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙኤል ካሳሁን፣ በአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ በተለያዩ መስኮች ዓውደ ጥናት በማዘጋጀት ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካል ጉዳተኞች ላይ ሙስና እንዴት እንደሚፈጸም ግንዛቤ ለመፍጠርና በፖሊሲ ሊካተቱ የሚችሉ ሐሳቦችንም ለማግኘት ዓውደ ጥናቱ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...