Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የታማኝ በየነ አቀባበል

ትኩስ ፅሁፎች

ከሁለት አሠርታት በላይ በውጭ አገር በስደት የቆየው አርቲስት ታማኝ በየነ ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመገኘት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አምባቸው መኰንን (ዶ/ር) ጨምሮ የመንግሥት ሹማምንት፣ ወላጅ እናቱ፣ ወዳጅ ዘመድና ከያንያን አቀባበል አድርገውለታል፡፡ በጎንደር ከተማ በ1955 ዓ.ም. የተወለደው ታማኝ በታዋቂው የጎንደር ፋሲለደስ ባህል ቡድን በአስተዋዋቂነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ በተመሳሳይ ሙያ ከመሥራቱ ሌላ በሕዝብ ለሕዝብ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ጉዞ ከአስተዋዋቂነቱ በተጨማሪ በከበሮ መቺነት ተጫውቷል፡፡ በስደት ከ22 ዓመታት በፊት ወደ አሜሪካ እስከተጓዘ ድረስ በጥበቡ ዘርፍ ሲሠራ የቆየው ታማኝ በስደቱ ወቅት ኢትዮጵያዊነትን በማቀንቀንና በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነቱም ይታወቃል፡፡ ታማኝ በቅርቡ በመንግሥት በተቋቋመው የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የመማክርት ጉባዔ አባል ሆኖ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መመረጡም ታውቋል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች