ጥሬ ዕቃዎች
- 75 ግራም ዓይብ
- ½ ኩባያ ካሮት የተከተፈ
- ¼ የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሾርባ ማንኪያ ሽንኩርት የተከተፈ
- ትንሽ ሚጥሚጣ
- የፐርስሜሎ ቅጠል
አዘገጃጀት
- ዓይብና ካሮት ማደባለቅ፤
- ጨው፣ ሚጥሚጣና ሽንኩርት ደብልቆ ውስጥ መጨመር፤
- በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተዘጋጀውን ድብልቅ በደንብ አዋህዶ የካሮት ቅርፅ እንዲይዝ አድርጎ ማድቦልቦል፤
- ቅርፁን እንዲጠብቅ በረዶ ቤት ውስጥ ማቀዝቀዝ፤
- የፐርስሜሎውን ቅጠል ከጫፉ በመሰካት ካሮት አስመስሎ ማቅረብ፡፡
ስምንት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)