Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊአፍሪካን ያሠጋው ቢጫ ወባ

አፍሪካን ያሠጋው ቢጫ ወባ

ቀን:

በአንጎላ የተከሰተው የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ትልቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ሰሞኑን አስታውቋል፡፡ ከታህሳስ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በአገሪቱ መታየት የጀመረውንና ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐና ዩጋንዳ የተስፋፋውን የቢጫ ወባ ወረርሽኝ ለመከላከል፣ በጄኔቫ ስዊዘርላንድ አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው ድርጅቱ፣ ወረርሽኙን የመከላከል ሥራ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

በአፍሪካ ከአንጐላ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ በኬንያ እንዲሁም ከእነዚህ አገሮች ባንዱ ቆይታ በነበረው ግለሰብ አማካይነት ቻይና የገባ ቢሆንም፣ ድርጅቱ አፋጣኝ ምላሽ የሚሻ ዓለም አቀፍ የጤና እክል አይደለም፣ በዓለም አቀፍ እርዳታ በየአገሮቹ የውስጥ አቅም ችግሩ መፈታት ይችላል ብሏል፡፡

ሲኤንኤን እንደዘገበው፣ በወረርሽኙ 2,400 ሰዎች የተጠቁ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 300 ሞተዋል፡፡ በሽታውም በፍጥነት የሚስፋፋና ገዳይ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

- Advertisement -

በአፍሪካ ባለፉት ሦስት አሠርታት ውስጥ ከተከሰቱ የቢጫ ወባ ወረርሽኞች፣ የአሁኑ አስከፊው ነው ተብሏል፡፡ በአንጐላ ሉዋንዳ ከአምስት ወራት በፊት የተከሰተው ወረርሽኝም አሁን ላይ፣ አገሪቱ ካላት 18 ከተሞች በ14ቱ ተዛምቷል፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ 50 የሚጠጉ የወረርሽኙ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከአንጐላ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ናቸው፡፡ ዩጋንዳ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ወባ ተዛምቶ፣ 60 ያህል ዜጐቿ ተጠቅተዋል፡፡ ኬንያና ቻይና ደግሞ ከእነዚህ አገሮች ወደየአገሮቹ በገቡ ዜጐች የወረርሽኙ ተጠቂ ሆነዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎችም ወረርሽኙ የቢጫ ወባ ባልተከተቡና ወረርሽኙ ከተገኘባቸው አገሮች በሚጐራበቱ አገሮች ይዛመታል የሚል ስጋታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

ቢጫ ወባን ከሚያስተላልፉት ሁለት ዓይነት የወባ ትንኞች አንዷ የዚካ ቫይረስንና የዳንጉ ፌቨርን ማስትላለፏም ችግሩን ውስብስብ እንዳያደርገው ተሰግቷል፡፡

ድርጅቱ በሽታውን ለመከላከል በተለይ አንጐላና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጐ በሚደረጉ ጉዞዎች ሁሉም ተጓዦች የቢጫ ወባ ክትባት እንዲወስዱ በተለይ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር የተያያዘ ሥራ ያላቸው እንዲከተቡ፣ የቁጥጥር ሥራ እንዲሠራና ለአደጋው ተጋላጭ ከሆኑ አገሮች የሚወጡና የሚገቡ ተጓዦች ክትባቱን መከተባቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ድርጅቱ አሳውቋል፡፡

ወባ በኢትዮጵያ ገዳይ ከሚባሉ በሽታዎች ከመጀመሪያዎቹ ይመደባል፡፡ አገሪቱ ካላት ሥነ ምህዳራዊ አቀማመጥ ጋር ተያይዞም 60 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ውስጥ ይኖራል፡፡ በመሆኑም መንግሥት ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የቁጥጥርና በሽታውን የመከላከል ሥራ እያከናወነ እንዲሁም ነፃ የአጐበር ስርጭት እያደረገ እንደሚገኝ፣ ዓለም አቀፉ የወባ ቀን ባለፈው ሚያዝያ ማብቂያ ላይ ሲከበር መገለጹ ይታወቃል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...