Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

ስለግንቦት 20 እና ‹ግንቦት› ወር አቋሜን ለጠየቃችሁኝ ጓደኞቼ ሐሳቤን የሚገልጸውን ቀጣዩን ጽሑፌን በድጋሚ ጋብዣችኋለሁ።

  1. ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ስመ ጥር መኮንን ነበሩ። ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግሥትን ድጋፍና ዕርዳታ እንድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ታዲያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው ዕረፍት እንኳን ሳያደርጉ ዓድዋ ድረስ ተጉዘው፣ በ1888 ዓ.ም. የካቲት 23 ቀን ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ገጥመው የጀግንነት ጀብዱ ፈጽመው በዚያው ዕለት ሕይወታቸው እዚያው ጦር ሜዳ ላይ አልፏል። እኚህ ሰው ‹‹የአገር ጀግና›› የሚል ስያሜ መለያቸው ሆኖ እስከ ዛሬ ስማቸው ይታወሳል።
  2. የእኚህ ታላቅ ሰው የአብራክ ክፋይ የሆኑት [ራስ] ደስታ ዳምጠው እንደ አባታቸው ሁሉ በርካታ መልካም ሥራዎችን ለአገራቸው ፈጽመው ሲያበቁ፣ በ1928 ዓ.ም. የጣሊያን ጦር አገራችንን ለሁለተኛ ጊዜ ሲወር በሶማሊያ በኩል ይመጣ የነበረውን ጦር በጀግንነትና በወኔ ዶሎ ድረስ ወርደው በመግጠም የጀግንነት ሥራ ቢሠሩም፣ ጦሩ በደረሰበት ሽንፈት ሠራዊታቸው ተበተነ። እሳቸው ግን በአርበኝነት ለአንድ ዓመት ያህል ሲፋለሙ ኖረው ጣሊያን እጅ ላይ ወደቁ። ጣሊያን እኚህን ታላቅ ጀግና የካቲት 16 ቀን 1929 ዓ.ም. በአደባባይ በጥይት ደብድቦ ገደላቸው። ራስ ደስታ በስማቸው መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባላቸው ‹‹ጀግና ሰው›› በመሆን ዛሬም ድረስ ይታወሳሉ።
  3. የእኚህ ታላቅ ሰው ልጅ የነበሩት [ሪር አድሚራል] እስክንድር ደስታ ደግሞ እንደ አባታቸውና እንደ አያታቸው ስኬታማ የአስተዳደርና የዲፕሎማሲ ሰው ነበሩ። የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ በመሆን ስኬታማ የነበሩት እኚህ ሰው፣ እናታቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጅ [ልዕልት ተናኜ ወርቅ] በመሆናቸው ብቻ ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም. ከ60ዎቹ ከፍተኛ ባለሥልጣናት መሀል አንዱ ሆነው በደርግ ጥይት ተደብድበው ተገደሉ።

ሦስተኛው ይባስ እንግዲህ ይህ ነው። እኚህ ሰው የሞቱት በአገራቸው ሲሆን ገዳያቸውም የአገራቸው ሰው ነው። እንደ አያታቸውና አባታቸው በጠላት እጅ ሳይሆን በአገራቸው በግፍ ተገደሉ። ታሪካቸውን ስናጤነው የአገሩን ልጅ የገደለው ደርግ ራሱ ጀግና አልተባለም። በአገራቸውም ሰው የተገደሉትም እስክንድር እንዲሁ። ምክንያቱም ‹‹ለአገሩ ሲል›› የአገሩን ልጅ የገደለ ጀግና አይባልም። ‹‹ለአገሩ ሲል›› በአገሩ ልጅ የተገደለም እንዲሁ።

‹‹ለአገሬ ስል ነው›› የሚል ሰው የአገሩን ልጅ የሚገድል ከሆነ ጀግና አይባልምና የታሪክ ተወቃሽ መሆኑ አይቀርም። ‹‹ለአገሬ ስል ነው›› ብሎ በአገሩ ልጅ የሚሞትም እንዲሁ። ሦስተኛው ይባስ በሉ። እርስ በርሱ እየተላለቀ ‹‹ለአገሬ ስል ነው›› የሚል ካለ ልቦና ይስጠው።

ታሪክ ማለት ዛሬ አልፎ ሲያረጅ እንጂ የጨበጥነው ዘመን እውነታ ለዘመኑ ባለው ጥቅም ብቻ የሚለካ አይደለምና፡፡ ዛሬ በሚሰጠን የጀግንነት ስያሜ አንፈንድቅ። ታሪክ አድሮ ይወቅሳል።

ፈጣሪያችን ሆይ! ጠላት ሲመጣ ተፋልመን ለአገራችን በክብር የምንሰዋ እንጂ፣ እርስ በርስ የምንተላለቅ ሕዝቦች ከመሆን አድነን!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

 (ያሬድ ሹመቴ፣ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...