ኢትዮጵያ ያነሳሳችውን የኤርትራና የጅቡቲ የእርቅ ስምምነት የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ እንደተቀበሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የመሩት የልዑካን ቡድን ወደ ኤርትራ ያቀናውም ይህንን ተጨማሪ ዓላማ ሰንቆ ነበር፡፡››
የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ኤርትራን ከጎበኘ በኋላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የኤርትራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኦስማን ሳሌህን ይዘው ወደ ጅቡቲ አቅንተው ነበር፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ በፌስ ቡክ ገጻቸው ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል መስማማታቸውን ገልጸው፣ የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡