አስፈላጊ
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በትልልቁ የተከተፈ የአበሻ ጐመን
- 2 ኪሎ ግራም በአጭር፣ በአጭሩ የተቆራረጠ የበግ፣ የበሬ ወይም የጥጃ የጐድን አጥንት
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ቀይ ሽንኩር
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
- 4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ዝንጅብል
- 3 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 1 የሾርባ ማንኪያ ነጭ ቅመም
- 2 የሾርባ ማንኪያ ጨው
- 2 የሾርባ ማንኪያ የመቀቀያ አፈር
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ ማቁላላት፤
- አጥንቱን በትንንሹ ቀርጥፎና አስተካክሎ ለብቻው ማብሰል፤
- ጐመኑን ለብቻው በመቀቀያ አፈር በጣም ሳይበስል ቀቅሎ ማውጣትና የተቁላላ ሽንኩርት ላይ ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
- አጥንቱን መጨመር፤
- ቅቤ፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ዝንጅብሉን ጨምሮ እንዲበስል መተው፤
- መረቅ እንዳይበዛ ተጠንቅቆ እያማሰሉ በመለስተኛ እሳት ማብሰል፤
- ነጭ ቅመምና ጨው አስተካክሎ ውኃው ሲመጥ ማውጣትና ቃርያ ጣል፣ ጣል አድርጐ ማቅረብ፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱሼፍ) «የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት» (2003)