Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዋሊያዎቹ ሙሉ ሦስት ነጥብ ያገኙበትን ውጤት አስመዘገቡ

ዋሊያዎቹ ሙሉ ሦስት ነጥብ ያገኙበትን ውጤት አስመዘገቡ

ቀን:

መስከረም 30 የኬንያ አቻቸውን በባህር ዳር ያስተናግዳሉ

ካሜሩን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ ስድስት ከጋና፣ ኬንያና ሴራሊዮን የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሴራሊዮን አቻውን 1 ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት የተሻለ መነቃቃት ይፈጥርለታል ተባለ፡፡ ውጤቱ መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ባህር ዳር ላይ ከኬንያ ጋር ለሚያደርገው ሦስተኛ የምድብ ማጣሪያ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆንም ይታመናል፡፡

ጳጉሜን 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የተደረገውን የኢትዮጵያና የኬንያ ጨዋታ የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱን ጨምሮ ሌሎችም የቡድኑ አጠቃላይ ቁመና ኳስን መሥርቶ ለመጫወት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑ እንደተጠበቀ፣ በሥነ ልቦናውና በአካል ብቃቱ ረገድ ግን አሁንም እንደሚቀረው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

አሠልጣኙ በሐዋሳ ባደረጉት ከአንድ ወር ያላነሰ የዝግጅት ጊዜ የቡድኑን አቋም መገምገም ይችሉ ዘንድ ያገኙት የወዳጅነት ጨዋታ አንድ ብቻ መሆኑ ጉዳት እንዳለው፣ ለወደፊቱ ግን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከይድረስ ይድረስ አሠራር ወጥቶ ዓለም የሚጠቀምበትን ከመደበኛ እስከ ወዳጅነት የውድድር መርሐ ግብሮችን ግምት ውስጥ አስገብቶ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት እየተነገረ ይገኛል፡፡ ዋሊያዎቹን የምድቡ ቡድኖች ሁለት ሁለት ጨዋታ አድርገው ሁሉም የሜዳ ተጠቃሚነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በመጀመርው የምድብ ጨዋታ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ወደ ጋና አምርታ 5 ለ0፣ ኬንያ ደግሞ ወደ ሴራሊዮን አቅንታና ጋና ደግሞ ወደ ኬንያ አምርታ ሽንፈትን አስተናግደዋል፡፡ በምድቡ የሚገኙት አራቱም በእኩል ሦስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው መቀመጣቸው ቀጣዩንና ሦስተኛውን የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ከባድ እንደሚያደርገውም እየተነገረ ይገኛል፡፡ በሜዳቸው የኬንያ አቻዎቻቸውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም መስከረም 30 የሚያደርጉት ዋሊያዎቹ፣ እንደ ዋና አሠልጣኙ በሐዋሳ የታየባቸውን የአካል ብቃትና የሥነ ልቦና ክፍተት አርመው ለወሳኙ ጨዋታ ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው ይታመናል፡፡

ከጋናው የሰፊ ግብ ሽንፈት በኋላ በአሠልጣኝ አብርሃም ተዘጋጅተው የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዋሊያዎቹ፣ ጥሩ ሁለተኛ ሆነው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ትኬት መቁረጥ የሚያስችላቸውን የመጀመርያውን ሦስት ነጥብ አግኝተዋል፡፡ በተለይ በሜዳቸው የሚያደርጓቸው ሁለት ጨዋታዎች እጅጉን ውድና ተፈላጊ መሆናቸው አሠልጣኝ አብርሃምና ተጨዋቾቻቸው ልብ ሊሉ እንደሚገባ ጭምር ሊያምኑ ይገባል፡፡

ከውጤቱ በኋላ ጨዋታው በአጠቃላይ ጥሩ እንደነበረ፣ ይሁንና አሠልጣኙ የሚሰጠውን ታክቲክ ሙሉ በሙሉ እንዳልተገበሩት ተናግረዋል፡፡ በአልባኒያ ስከንደርቡ በመጫወት ከፍተኛ ዕውቅና እያተረፈ የሚገኘው ቢኒያም በላይ ይህንኑ የሚያጠናክር አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ በተለይም ቡድኑ የሚያገኛቸውን መልካም አጋጣሚዎች ወደ ውጤት በመለወጥ ረገድ ሰፊ ክፍተት መኖሩ፣ በቀጣይ እነዚህን የመሰሉ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍሉ ድክመቶች ሊታረሙ እንደሚገባ ጭምር አስረድቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...