Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልመልካም አዲስ ዓመት!

መልካም አዲስ ዓመት!

ቀን:

ጤና ይስጥልኝ፡፡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር እባላለሁ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም  አዲስ ዓመት ለራሳችን፣ ለቤተሰቦቻችን  እንዲሁም ለወዳጆቻችን  ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው፡፡   ይህ ተስፋ በኢትዮጵያ ከቀደሙት ዓመታት ይልቅ ዘንድሮ ይበልጥ ለምልሞ ይታያል፡፡  በአገራቸው እየታየ ባለው አዲስ ራዕይ የተደመሙ ኢትዮጵያውያን፣  በለውጡ ሰላማዊ  አካታችና የበለፀገች ኢትዮጵያን  እንደሚያልሙ  እሰማለሁ፡፡

ስለ አዲስ ዓመት ሳስብ ኢትዮጵያውያንና መንግሥታቸው ለለውጡ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ በውስጤ የሚመላለሰውን ዓይነት ጥንካሬ፣ ተስፋና አዎንታዊነትን የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ አዲስ ዓመት ታላቅ ተስፋና ዕድልን ይዞ ቢመጣም ስለቀጣይነቱ ምንም ዓይነት ዋስትና አይሰጠንም፡፡  የተሻለ ነገን መገንባት፤ ከተስፋ በላይ የሆነ ሥራን ይጠይቃል፡፡

ህልማችን መጪው ጊዜ  ለኢትዮጵያ ካለፉት ዓመታት የተሻለ  እንዲሆን ከሆነ  ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡   ግልጽ፣ ገንቢ አንዳንዴም አስቸጋሪ ውይይቶችን ማካሄድ ይኖርብናል፡፡ ሰዎች ተመሳሳይ ግብ  ቢኖራቸው እንኳ ወደ ስኬት የሚያደርሳቸው የየራሳቸው የተለያየ ሐሳብ እንደሚኖራቸው መቀበል ይኖርብናል፡፡

በተመሳሳይ ከአንድነት ይልቅ በሰዎች መካከል ክፍፍልን ከሚጋብዙና በተሳሳተ መንገድ አመጽን ከሚያበረታቱ ሐሳቦች በተቃራኒው መቆም ይኖርብናል፡፡  እንዲሁ ስለ ተግዳሮቶች ከማውራት ይልቅ ብዙ መሥራትም ይጠበቅብናል፡፡  ትኩረታችንን መፍትሔ ማፈላለግ ላይ ማድረግ ይኖርብናል፡፡

የምንፈልገውን አዎንታዊ ለውጥ ዕውን ለማድረግ እያንዳንዳችን የየድርሻችንን መወጣት አለብን የሚለውን ሐሳብ በደንብ መቀበልም ይጠይቃል፡፡ 

በአሜሪካ አዲስ ዓመት መባቻ ላይ ቃል የምንገባበት ባህል አለን፡፡ እኩለ ሌሊት ላይ ከአሮጌው ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገራችን ሲበሰር ሁላችንም  ለየራሳችን በዓመቱ የተሻለ ነገር ለመከወን ቃል እንገባለን፡፡ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ለመከተል አዲስ ክህሎት ወይም ለሌሎች መልካምን ለመዋል ሊሆን ይችላል፡፡

የምንመኘውን የተሻለ ነገ ለማሰብም ሆነ በጥረታችን ዕውን ለማድረግ የአዲስ ዓመት ቃል ኪዳን ትልቅ ዕድልን ይፈጥራል፡፡ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ የራሳቸውንም ሆነ የሌሎችን ሕይወት ለመቀየር የሚያስችል ጥረት ለማድረግ ቃል እንዲገቡ አበረታታለሁ፡፡ በጋራ ለተሻለ ነገ የምንሠራ ከሆነ ከዓምናው ዘንድሮ በእርግጠኝነት የተሻለ ይሆናል፡፡

ኤምባሲው ለኢትዮጵያ ቀጣይ ስኬትና ለሁለቱ አገሮች የበለጠ ጠንካራ አጋርነት የበኩሉን ለመወጣት ትልቅ ፍላጎትና ዝግጁነት አለው፡፡  ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚገባቸውን የተሻለ ነገ ለመፍጠር ኤምባሲው ማድረግ አለበት የምትሉትን እንዲሁም እናንተ አየተወጣችሁ ያላችሁትን ነገር ለመስማት ዝግጁ ነኝ፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የብልፅግናና የደስታ እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

መልካም አዲስ ዓመት!

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...