Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአራት ክልሎች ከስምንት ሺሕ በላይ የወንጀል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

በአራት ክልሎች ከስምንት ሺሕ በላይ የወንጀል ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

ቀን:

በፌዴራል በዓልን አስመልክቶ የተደረገ ይቅርታ የለም

በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ክስ ተመሥርቶባቸው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው፣ የእስራት ቅጣት ተጥሎባቸው በመታረም ላይ ለነበሩ 8,875 ፍርደኞች አራት ክልሎች ይቅርታ አደረጉ፡፡

የ2011 ዓ.ም. አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለታራሚዎች ይቅርታ ያደረጉት ክልሎች የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የቤኒሻጉል ጉሙዝና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥታት ናቸው፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ታራሚዎች ይቅርታ ያደረገው የኦሮሚያ ክልል ሲሆን፣ ለ5,325 ፍርደኞች ይቅርታ አድርጓል፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በተላለፈ ውሳኔ መሠረት በይቅርታ እንዲለቀቁ መደረጋቸውንና ዕርምጃው የተወሰደው አዲሱን ዓመት በሰላምና በፍቅር ለመቀበል ካላቸው እሳቤ መሆኑን፣ የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የክልሉ መንግሥት ከ40 ሺሕ በላይ ታራሚዎችን በይቅርታ መልቀቁን አክለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ክልል መንግሥትም ለ3,000 ታራሚዎች ይቅርታ በማድረግ ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉን፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ ተናግረዋል፡፡ የጋምቤላ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ ኮሚሽነር ቲቶ ኃዋርያ እንዳስታወቁት፣ የክልሉ መንግሥት ይቅርታ ያደረገላቸው 370 ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥትም ለ188 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ ኮሚሽነር አዲሱ ሐተሴም ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ለበርካታ ታራሚዎች ይቅርታ እንደሚያደርግ በርካታ የታራሚዎች ቤተሰቦች የጠበቁ ቢሆንም፣ ‹‹በተቀመጠው መሥፈርት መሠረት ለታራሚ ይቅርታ የሚደረገው ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ የተቀመጠውን መሥፈርት አሟልቶ በተገኘበት በማንኛውም ጊዜ ነው፤›› በማለት፣ በአዲስ ዓመት በይቅርታ የሚለቀቅ ፍርደኛ እንደሌለ ያስታወቁት የፌዴራል የይቅርታ ቦርድ ዳይሬክተር አቶ ዘለቀ ደሌሎ ናቸው፡፡

ቦርዱ በዓመቱ ውስጥ ይቅርታ ሲያደርግ መቆየቱንና ወደፊትም ሁኔታዎች እየታዩ፣ ታራሚዎችን በመገምገም መሥፈርቱን አሟልተው ሲገኙ ይቅርታ እንደሚያደርግ በመግለጽ፣ በአዲስ ዓመት መግቢያ የሚለቀቁ ፍርደኞች እንደሌሉ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ ዓመት መግቢያን ምክንያት በማድረግ ክሳቸው የሚቋረጥ ተጠርጣሪዎች ስለመኖራቸው ሪፖርተር የጠየቃቸው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዬ ደንደአ፣ ባለፉት ወራት ሁኔታዎች እየታዩ የበርካታ ተጠርጣሪዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ወደፊትም እየታየ የሚቀጥል ከሚሆን በስተቀር፣ በአዲስ ዓመት ምክንያት የሚቋረጥ ክስ እንደሌለ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...