Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፒያሳ በግጭት ሲረበሽ ውሏል

ፒያሳ በግጭት ሲረበሽ ውሏል

ቀን:

ከአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጡ ወጣቶችና ፒያሳ አካባቢ ባሉ ወጣቶች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አካባቢው ተረብሾ ውሏል፡፡

በተለያዩ አውቶብሶች ፒያሳ መሀል ላይ የተበተኑ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ወጣቶች ገጀራና ሚስማር የተመታበት እንጨት ይዘው እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን፣ የፒያሳ አካባቢ የማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያን ለመዝረፍ እንቅስቃሴ መደረጉንና ፖሊሶችም በጥይት መበተናቸውን፣ ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡

የፒያሳ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተረኛ መኰንን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ 700 የሚሆኑ ወጣቶች ጭነው የመጡት መኪኖች በአካባቢው ወጣቶችና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሪፖርተርም ፖሊስ ጣቢያው ውስጥ ተገኝቶ፣ በአማርኛ መግባባት የማይችሉ ጉዳት የደረሰባቸው ወጣቶች የሕክምና ዕርዳታ ሲጠብቁ ለማስተዋል ችሏል፡፡

በዳግማዊ በአፄ ምንልክ አደባባይ ሐውልትና አካባቢም በመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የነበረ ሲሆን፣ የፌዴራል አድማ በታኝ ፖሊስም ወደ አመሻሹ አካባቢ ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ወደ ጎዳና የወጡ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ሲበትን ተስተውሏል፡፡

በፒያሳ የሚገኙ ባንኮችና የንግድ መደብሮች ሙሉ በሙሉ ከመዘጋታቸውም በተጨማሪ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትም በመቋረጡ ብዙዎች ሲቸገሩ ታይተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...