ነገ በሚሌኒየም አዳራሽ ሊካሄድ የነበረው የቴዲ አፍሮ ‹‹ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር›› ኮንሰርት ለሚቀጥለው ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ተላለፈ፡፡
የድምፃዊ የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ማኔጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንሰርቱ ለሚቀጥለው ሳምንት እንዲተላለፍ ያቀረበውን ጥያቄ ድምፃዊ ቴዎድሮስም ተቀብሎታል፡፡
ኮንሰርቱ እንዲተላለፍ የተደረገውም በነገው ዕለት የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ውስጥ ስለሚገቡና በርካታ ደጋፊዎች አመራሮቹን ለመቀበል ስለሚወጡ፣ ከተማው የሚጨናነቅና ውክቢያም ሊፈጠር ይችላል ከሚል ሥጋት አኳያ መሆኑ ታውቋል፡፡ በቀጣይ ሳምንት ኮንሰርቱ በደመቀና ሁሉም በሚሳተፍበት ሁኔታ ሊካሄድ ስለሚችል ድምፃዊ ቴዎድሮስና ሁሉም የኮንሰርቱ አዘጋጆች በደስታ ተቀብለውት መተላለፉን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡