Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናኢሶዴፓ ቀጣይ ምርጫዎች ከመደረጋቸው በፊት ውይይት እንዲቀድም አሳሰበ

ኢሶዴፓ ቀጣይ ምርጫዎች ከመደረጋቸው በፊት ውይይት እንዲቀድም አሳሰበ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) አገራዊ ቀጣይ ምርጫዎች ከመደረጋቸው በፊት ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲደረግ አሳሰበ፡፡

የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻውና አመራሮች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ስለምርጫ ውድድር ሒደቶች፣ ስለገለልተኛ ታዛቢዎች፣ ስለነፃነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተዓማኒነትና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተግባራዊ ስለሚሆንበት ሕግና አሠራር ተገቢው ውይይትና ድርድር ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረስ አለበት ብለዋል፡፡

በአገሪቱ መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የተራራቁ ሐሳቦችን የሚያራምዱ ኃይሎች፣ የሐሳብ ልዩነቶቻቸውን ለማቀራረብና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱም ሆነ፣ በምን ዓይነት ሁኔታ አማራጭ ሐሳባቸውን ለሕዝብ አቅርበው በሕዝብ ውሳኔ ዕልባት እንዲያገኝ እንደሚያደርጉ በግልጽ አለመቀመጡን ጠቁመዋል፡፡

- Advertisement -

ተግባራዊ እንቅስቃሴም በወቅቱ እየተካሄደ ባለመሆኑ መሠረታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ተገቢ ድርድሮች መደረግ እንዳለባቸው፣ ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስና በልዩነት በሚቀመጡ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ዕልባት የሚሰጥበት ሒደት በአስቸኳይ መጀመር እንዳለበትም አቶ ጥላሁን አሳስበዋል፡፡

የተጀመረው የለውጥ ሒደት የተሳካና ዘላቂ እንዲሆን በአንድ ፓርቲ ካድሬዎች ብቻ እንዲመራ ማድረግ አስቸጋሪና የማያዋጣ መሆኑ በተግባር እየታየ ስለሆነ፣ የሚመለከታቸው የፖለቲካ ኃይሎች ድርሻቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚችሉበት የብሔራዊ አንድነት መንግሥት እንዲመሠረትም ጠይቀዋል፡፡

አቶ ጥላሁን ጨምረው እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ብዙ የሚበረታቱ ለውጦች ታይተዋል፡፡ ኢሶዴፓም የሚደግፋቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ወይም አካባቢዎች፣ በተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ሲፈጸሙ የቆዩ ጥቃቶች በብዙ አካባቢዎች አሁንም ያላቋረጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የብዙ ዜጎች ሕይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙንም አስረድተዋል፡፡ ሕዝቡ በሰላም ኑሮውን ለመምራትም ሆነ በነፃነት ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር የሚችልበት አስተማማኝ ሁኔታ አለመፈጠሩን፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በሥራ ቦታዎችና በየመንገዱ ጥቃት የሚያደርሱ ፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ፣ መንግሥት ተገቢውን ሕጋዊ ዕርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነት እንዲያረጋግጥም ጠይቀዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...