Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የአዲሱን የቡና ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹመት አፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ብሔራዊ ባንክ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ ዓለማየሁ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ከቦርዱ የቀረበለትን ጥያቄ በማየት ሹመታቸውን ማፅደቁ ተገለጸ፡፡

ከቡና ኢንተርናሽናል ባንክ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ ሙሉጌታ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ በቦርዱ ታጭተው የብሔራዊ ባንክን ውሳኔ ሲጠባበቁ ነበር፡፡

ብሔራዊ ባንክ የአቶ ሙሉጌታ ሹመት ከማፅደቁ በፊት ከመስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት መሰየማቸው አይዘነጋም፡፡

አቶ ሙሉጌታ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ታደሰ ጭንቅልን ተክተው ነው፡፡ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አቶ ሙሉጌታን ሲሾም፣ አቶ ታደሰ ደግሞ የባንኩ አማካሪ እንዲሆኑ ሰይሟቸዋል፡፡ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው አቶ ታደሰ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር ዕውቅና ከተሰጣቸው ሦስት የባንክ ባለሙያዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አዲሱ የቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ19 ዓመታት ያገለገሉ ናቸው፡፡ እንደ ባንኩ መረጃ አቶ ሙሉጌታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሠርተዋል፡፡ በተለይ ወደ ቡና ባንክ ከመምጣታቸው በፊት በቺፍ ቢዝነስ ኦፊሰርነት አጠቃላይ የባንኩን እንቅስቃሴ በመምራት ስትራቴጂውን በመቅረጽ፣ ዘመናዊ የሥራ ሒደቶችን  በመንደፍፖሊሲና መመርያዎችን በማዘጋጀት የባንኩን ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን አድርገዋል፡፡

ቀደም ሲልም በምክትል ፕሬዚዳንትነት የደንበኞች አካውንትና ትራንዛክሽን አገልግሎት ላይ የሠሩ ሲሆን፣ በምክትል ፕሬዚዳንት የፋይናንስ ዘርፉንም እንደመሩ የሥራ ልምዳቸው ያሳያል፡፡

አቶ ሙሉጌታ የባንኩ ቺፍ ሪስክና ኮምፖሊያንስ ኦፊሰር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአካውንት አናሊሲሲ በሥራ አስኪያጅነት፣ በብድር ኦዲት ቡድን መሪነት፣ በብድር ሞኒተሪንግ ኦፊሰርነት የሥራ ልምድ እንዳላቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በቦርድ አመራርነትም በርካታ ድርጅቶችን እንደመሩ የሚያመለክተው የአቶ ሙሉጌታን የሥራ ልምድ የሚያሳየው መረጃ፣ የኮሜርሽያል ኖሚኒስ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ማገልገላቸው በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ የሲዳ ቴክስታይል ቦርድ ሰብሳቢ፣ የኢትዮጵያ ህዳሴ፣ የኢትዮጵያ ኮሞዲቲ ኤክስቼንጅና ሌሎችንም ድርጅቶች በቦርድ አመራርነት ማገልገላቸው የሥራ ልምዳቸው ያስረዳል፡፡

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በኢንዱስትሪው ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ከሚገኙ የግል ባንኮች አንዱ ነው፡፡ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለ ዘጠኝ ዓመታት የቆየ ሲሆን፣ ከባንኩ ምሥረታ ማግሥት የመጀመርያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሲመሩ የቆዩት አቶ ነገደ አበበ ናቸው፡፡ ከዚያም በመቀጠል አቶ እሸቱ ፋንታዬና ሦስተኛው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ጭንቅል ሲሆኑ  አቶ ሙሉጌታ አራተኛው ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ናቸው፡፡

ቡና ባንክ 175 በላይ ቅርንጫፎችን በመላ አገሪቱ የከፈተ ሲሆን፣ የባለአክሲዮኖች ቁጥር 13 ሺሕ በላይና የካፒታል መጠኑም 1.5 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ከባንኩ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች