የሆሄ ግድፈት በመጣጥፍ፣ በድርሰትና በተለያዩ የንግድ ስሞች ላይ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ሆኖም በትላልቅ ኢንዱስትሪዎች መለያ (ብራንድ) ላይ ያጋጥማል ማለቱ ይከብዳል፡፡ ቢቢሲ እንደሚለው ግን በሆንግ ኮንግ መቀመጫውን ያደረገው ካቲ ፓስፊክ በአውሮፕላኑ ጎን ላይ በጻፈው መለያ የሆሄ ግድፈት ፈጽሟል፡፡
<<CATHAY PACIFIC>> በሚል የሚጠራው ጄት ፓስፊክ በሚለው ላይ ‹‹ኤፍ›› የተገደፈች ሲሆን፣ መገደፏ የታወቀው ጄቱ ሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ካረፈ በኋላ ነበር፡፡
የፊደል ግድፈቱ የታወቀው ደግሞ በካምፓኒው ባለቤቶች ሳይሆን የንስር ዓይን አላቸው ተብለው በተሞካሹ ተሳፋሪዎች ነው፡፡ የአውሮፕላኑ የፊደል ግድፈት እንዲታረምም መልሶ ወደ ጋራዥ ገብቷል፡፡
*******