Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልአበባን ተቀዳጅ እና መስከረም 10

አበባን ተቀዳጅ እና መስከረም 10

ቀን:

ክረምቱ ሊወጣ ከሚንደረደርበት በጥቢው የመስከረም ወር 10 ቀን ዋዜማ ላይ እንገኛለን፡፡ ‹‹አበብዬ አበባዬ መስከረም ጠባዬ›› በሚለው ዝማሬና ጨዋታ ባለመወሰን ‹‹አበባን ተቀዳጅ›› በግዕዙ ጥሪ ‹‹ተቀጸል ጽጌ›› እየተባለ ኅብረተሰቡ አበባ ከሚቀባበልበት መስከረም 10 ቀን ላይደርሷል፡፡

1500 ዓመት በፊት አበባን ተቀዳጅ የሚል ትርጉም ያለው የተቀጸል ጽጌ ክብረ በዓል መከበር የተጀመረው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን፣ ዝማሬውን ያዘጋጀው ደግሞ ቅዱስ ያሬድ ነበር፡፡ ክረምት በሚወጣበት መስከረም 25 ቀን የአበባው በዓል ሲከበር ቅዱስ ያሬድ ንጉሠ ነገሥቱን ‹‹ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐፀጌ›› – አፄ ገብረ መስቀል ክረምቱ አልፎልሃልና አበባን ተቀዳጅ፣ አበባን ተላበስ እያለ ያወድሰው የነበረው በዓላዊ ትውፊት እየተቀባበለ እስከ 15ኛው ምዕት ዓመት ደርሶ ነበር፡፡

 በአፄ ዳዊት ዘመን የጌታችን ግማደ መስቀሉ መስከረም 10 ቀን አገር ቤት በመድረሱ ግማዱም በንጉሡ ምክንያት በመምጣቱ ‹‹አፄ መስቀል›› እየተባለ መከበር ሲጀምር፣ 25ኛው ቀን የአበባው በዓልም 15 ቀን ወደኋላ በማፈግፈግ ከርሱ ጋር ባንድነት እንዲከበር በመወሰኑ እስካሁን በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን (1923-1967) 1966 መስከረም 10 ድረስ በዓሉ ቀድሞ በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት፣ በኋላም በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ይከበር ነበር፡፡ በዘመነ ደርግ ተቋርጦ የነበረው የአበባው በዓል ተቀጸል ጽጌ፣ 1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዐውደ ምሕረት በመንፈሳዊ ሥነሥርዓትና ለምዕመኑም ሆነ ለኅብረተሰቡ አበባ እየታደለ መከበር ጀምሮ እንደቀጠለ ነው፡፡

ክረምቱ አልፎ የጥቢው መዛለቂያ የመፀው (አበባ) ወቅት (ስፕሪንግ) መስከረም 26 ቀን ላይ እንቀበላለን፡፡ በአንድ ድርሳነ አበባ እንደተገለጸው፣ ‹‹የክረምቱ ወራት አልፎ መጸው ብሎም በጋው ሲተካ፣ ምድር በልምላሜ ፀጋ ተውባ አረንጓዴ ልብስ ተጎናጽፋ፣ በዕፀዋት አበባ ደምቃ፣ የመንፈስ ደስታ የምታድልበት፣ ሰማይ በከዋክብት አጊጦና አሸብርቆ የሚታይበት በመሆኑ የአበባ በዓል ስም ከግብር የተስማማለት ነው፡፡››

በተለያዩ አገሮች እንደየመልክዓ ምድራቸው የአበባ በዓልን በአገር ደረጃ ያከብሩታል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለም ገበያ ውስጥ የኢትዮጵያ አበባ ገበያውን እየተቆጣጠረ ባለበት ሁኔታ ነባሩ ትውፊታዊና ባህላዊ የአበባ በዓል አከባበራችንን አጠናክረን ማክበር የምንጀምረው መቼ ይሆን? ነው ወይስ እንደ ፍቅረኞች ቀን የአበባ በዓሉንም ከውጭ ልናስመጣ ነው? የአበባ ማኅበራትና አበባና ዕፀዋት ላይ የሚያተኩሩ መንግሥታዊ ተቋማት ወደራሳችን ትውፊቶች የሚመለሱበት ጊዜ መቼ ይሆን?

ስለ ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር (ባሕረ ሐሳብ) ጥንታዊ ማስረጃ የሚገኝበትመጽሐፈ ድጓ ድርሰት በአራቱ ወቅቶች (ክረምትና መፀው፣ በጋና ፀደይ) ተመሥርቶ የተዘጋጀ ነው፡፡ በወቅቶቹ ባሕርያት ላይ ተመሥርቶ ያሬድ ከደረሳቸው መካከል ለአብነት ያህል የክረምትና የመፀው ድርሰቶቹን እነሆ፡፡

በየዓመቱ መስከረም 26 ቀን የሚብተውን (የሚጀምረውን) ከክረምት በኋላ የሚመጣውን መፀው (የአበባ ወቅት) እንዲህ ገልጾታል፡፡ ‹‹በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት›› በጊዜው አለፈ አሁን የበረከት ጊዜ ይሆናል አበቦችም ያብባሉ፡፡

ሰኔ 26 ቀን የሚብተውን የኢትዮጵያ ክረምትንም ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናብ፣ ሶበ ይዘንብ ዝናብ ይትፌስሑ ነዳያን፤ ደምፀ እገሪሁ ለዝናብ፣ ሶበ ይዘንብ ዝናብ ይፀግቡ ርሁባን›› – የዝናብ ኮቴ ተሰማ፤ ዝናብ በዘነበ ጊዜ ነዳያን ይደሰታሉ፤ ርሁባንም ይጠግባሉ፡፡

ክረምት በሚወጣበት መስከረም 25 ቀን በአክሱም ታላቅ ሥነ በዓል ‹‹ተቀጸል ጽጌ›› (አበባን ተቀዳጅ) ይከበር ነበር፡፡ በዓፄ ገብረመስቀል ዘመን ሲከበር የተገኘው ቅዱስ ያሬድ ‹‹ተቀጸል ጽጌ፣ ገብረ መስቀል ዓፀጌ›› ብሎ ዘምሮ ንጉሡን እንዳስደሰታቸው ይወሳል፡፡ ይህ የአበባ በዓል እስከ 15ኛው ምዕት ዓመት ድረስ በዕለቱ ሲከበር ቆይቶ በአፄ ዳዊት ዘመን የእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል መስከረም 10 ቀን ኢትዮጵያ መድረሱን ተከትሎ በዓሉ ‹‹ተቀጸል ጽጌአፄ መስቀል›› በመባል ከመስከረም 25 ወደ መስከረም 10 ተዛውሮ እስካሁን በቤተ ክህነት ተወስኖ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ተቀጸል ጽጌን እንደ ቀደመው ዘመነ አክሱም ክረምት በሚወጣበት መስከረም 25 ማክበር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በየዘመኑ የሚያነሱ አሉ፡፡፡

‹‹የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ›› ደራሲ እጓለ ገብረ ዮሐንስ (/) ያሬድና የኢትዮጵያ ሥልጣኔ በሚለው ጽሑፋቸው የቅዱስ ያሬድ ተቀጸል ጽጌን ጨምሮ ልዩ ልዩ ትሩፋቱን አስመልክቶ እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹በአፍሪካ ምሥራቃዊ ዳርቻ የታወቀውን ሥልጣኔ ለማስገኘት ብዙ ሊቃውንት ጥረዋል፡፡ ሰማዩ ወይም ጠፈሩ ልሙጥ ነበር፡፡ የነዚህ ሰዎች ጥረት የሚያበሩ ከዋክብት በዚህ ጠፈር ላይ አስገኝቶአል፡፡ ምን ይሆናል ብዙ ደመና ሸፍኖቸአዋል፡፡ እነሱን ለመረዳት ክንፍ፣ ብርቱ የሕሊና ክንፍ ያሻል፡፡ ከማኅበረ ሊቃውንት አብነት ወይም ምስለኔነት ያለውን እንመርጣለን፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘመናት መካከል ለነበሩት ሁሉ የአገራችን ሊቃውንት እንደራሴነት ያለው ትልቅ መንፈስ ነው ብለን እናምናለን፡፡››

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...